በተማሪዎች የአማርኛ ትምህርት የማንበብና የመፃፍ ክሂሎች ላይ የመምህራን ቃላዊና ፅሁፋዊ ምጋቤምላሽ አቀራረብ ትንተና (በምስራቅ ጉራጌ ዞን ኬላ ወረዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2016

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በተማሪዎች የአማርኛ ትምህርት የማንበብና የመጻፍ ክሂሎች ላየመምህራንን ቃላዊና ጽሁፋዊ ምጋቤምላሽ አቀራረብ መተንተን ነው፡፡ ተጠኝዎቹም በምስራቅጉራጌ ዞን ኬላ ወረዳ 2ኛ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ አምስት መምህራን ሲሆኑ በጠቅላይእና 70 ተማሪዎች በእጣ ናሙና ተወስደዋል፡፡ 55ቱ ተማሪዎች የጽሁፍ መጠይቁን በአግባቡሞልተው መልሰዋል፣ በመሆኑም በትንተና ክፍሉ የተካተቱት እነዙህ ብቻ ናቸው፡፡ የጥናቱንዓላማ ለማሳካትም በሰነድ ፍተሻ፣ በምልከታ፣ በቃለመጠይቅና በጽሁፌ መጠይቅ መረጃዎችተሰብስበው፣ በአይነታዊ እና በመጠናዊ መተንተኛ ዘዴዎች በአፅንኦት ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱግኝትም የቋንቋ መምህራን የማንበብና መጻፍ ክሂሎችን ሲያስተምሩ ሁሉንም የምጋቤምላሽዓይነቶች እየቀያየሩ ወይም አንዱን ከአንዱ ጋር እያጣመሩ በሚገባ መጠቀም አለመቻላቸውን፣ብዙውን ጊዜ የግልና የብጤ (ጓደኛ) ምጋቤምላሾችን በመጠቀም ምጋቤምላሽ እንደማይሰጡ እናበምጋቤምላሽ አሰጣጥ ወቅት ማስረጃዎችን እንጂ ደጋፊ ምልክቶችን እንደማይጠቀሙ እናየመምህራን ምጋቤምላሽ አቀራረብ የተለያየ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ከጥናቱ መሰረታዊግኝቶች በመነሳት አስተያየቶችንማቅረብ የተቻለ ሲሆን የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ለአራቱምየምጋቤምላሽ ዓይነቶች ትኩረት ሰጥተው ለተማሪዎች የሚገባቸውን ምጋቤምላሽ እኩል ሊባልበሚችል ደረጃ ቢሰጡ፣ መምህራን ለገምጋሚ ምጋቤምላሽ ዓይነት ትኩረት በመስጠት ክፍልውስጥ ምጋቤምሊሻቸውን ማቅረብ ቢችሉ፣ ምጋቤምላሽ በሚሰጡበት ወቅት የመሰላቸትናየድካም ስሜት በአንዳንድ መምህራን የተስተዋለ ስለሆነ በይበልጥ የማንበብና የመጻፍክሂሎችን በሚያስተምሩበት ወቅት ድካማቸውን ሊያስወግድ የሚችሉ ዘዴዎችን ቢያመቻቹየሚሉት ቀርበዋል፡፡

Description

Keywords

አማርኛ ትምህርት የማንበብና የመጻፍ ክሂሎች

Citation