ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአራቱ ሃይማኖቶች የአማርኛ መዝሙራት ግጥሞች

dc.contributor.advisorዶ/ር የወንድወሰን አውላቸው
dc.contributor.authorየማርያምወርቅ ተሻገር
dc.date.accessioned2023-12-25T07:43:46Z
dc.date.available2023-12-25T07:43:46Z
dc.date.issued2022-06
dc.description.abstractይህ ጥናት “ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአራቱ ሃይማኖቶች የአማርኛ መዝሙራት ግጥሞች ውስጥ” በሚል ርእስ የተሠራ ነው፡፡ እነዚህም ሃይማኖቶች የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሔድ ቤተ ክርስቲያን፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት ሃይማኖቶች ናቸው፡፡ በእነዚህ መዝሙራት ውስጥ ያለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የተመለከቱ ጉዳዮች ተተንትነውበት የተሠራ ጥናት ነው፡፡ ጥናቱ ዓላማ አድርጎ የተነሣው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአራቱም ሃይማኖቶች የመዝሙር ግጥሞች እንዴት እንደቀረበ ለመፈተሽ ነው፡፡ ጉዳዩን የተመለከቱ ዝማሬዎችን ሰብስቦ በርእሰ ጉዳዮቻቸው በመባደን ይዞታቸውን እያብራራ አስፍሯል፡፡ ይህ ዓላማ ግቡን እንዲመታ በአራቱም ሃይማኖቶች ውስጥ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ መዝሙራት የትኞች ናቸው? ምን ብለው ነው ያነሡት? ምንስ ፊይዳ ነበራቸው? የሚሉ ጥያቁዎችን በማንሣት ጥናቱ የሚፈልገውን መረጃ እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ የጥናቱ ወሰንም ጉደዩን የተመለከቱ መዝሙሮቹ፣ ነሽዳዎች፣ መንዙማዎች ከ1983 ሰኔ እስከ 2013 ነሐሴ የተሠሩትን ያካትታል፡፡ መዝሙሮቹ በተለይ በኢህአዲግና በብልጽግ የአስተዳደር ዘመን የተዜሙ ሲሆኑ በመንፈሳዊ መዝሙር ውስጥ የተለያዩ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ጉዲዮች ውስጥ እንዴት እንደቀረቡ በመተንተን ድምፀታቸውን ያጠና ነው፡፡ በጥናቱ ከርእሰ ጉዲዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ቀዳማይና ካልአይ የመረጃ ምንጮች ተካተውበታል፡፡ በዋናነት የተጠቀመው የመረጃ ምንጭ በሰነድ ምርመራ የተገኙ መረጃዎችን እንደአስፈላጊነቱ ተጠቅሟል፡፡ ለሰበሰብኩት መረጃ መተንተኛ የንድፈ ሐሳብ ማሕቀፍች ብዬ የተጠቀምባቸው ተግባራዊ ወይም ጠቀሜታዊ ሲሆን ሁለተኛው ማኅበራዊ ሂስ ነው፡፡ የመተንተኛ ስሌቱ ዯግሞ የይዘት ትንተና (content analysis) ነው፡፡ የሰበሰብካቸው 1900 መዝሙራት መካከል ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያጠነጥኑ 49 መዝሙራትን አግኝቻሁ፡፡ ይህም ያነሣሁትን ርእሰ ጉዳይ በቀጥታ ሊያገዝፉልኝ የሚችሉትን ብቻ የተመለከተ ነው፡፡ መዝሙራቱ በአጥኚው ሲቃኙ በመዝሙሮቻቸው የምእመናኑን መሻትና ብሶት፣ ሕዝባቸው እና ሀገራቸው ከፈጣሪያቸው ጋር ያላቸውን የግንኙነት ለሥላሴና ሽክረት በዘመን መንፈስ ውስጥ በልዩ ልዩ ድምፀት ያለ ፍርሃት ገልጸዋል፡፡ መዝሙሮቹ፣ ነሺዲዎቹ፣ መንዙማዎቹ በኢህአዲግ ብልጽግና ሥርዒተ መንግሥት ጊዜ የቀረቡ በመሆናቸው የየዘመኑን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ክሥተቶችን ምን ነበርነትን እና ምን አለነትን ያሳዩ የዘመኑ የሕዝብ ድምፅ ሆነው በጥናቱ አገልግለዋል፡፡
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1159
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.subjectአራቱ ሃይማኖቶች ፡የመዝሙር ግጥሞች
dc.titleኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአራቱ ሃይማኖቶች የአማርኛ መዝሙራት ግጥሞች
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
የማርያምወርቅ ተሻገር.pdf
Size:
1.6 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: