በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሂደት የመምህራኑ የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና የክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበሩ ተዛምዶ (የካ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ሶስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ የተደረገ ጥናት)

dc.contributor.advisorአማረ, ጌታሁን (ፕሮፌሰር)
dc.contributor.authorመንግስቱ, መሰሉ
dc.date.accessioned2020-08-07T08:41:00Z
dc.date.accessioned2023-11-09T04:04:38Z
dc.date.available2020-08-07T08:41:00Z
dc.date.available2023-11-09T04:04:38Z
dc.date.issued2012-06
dc.description.abstractየዚህ ጥናት ዋና አላማ በአማርኛ ቋንቋ መምህራን የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና በክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበሩ መካከል ተዛምዶ መኖሩን መመርመር ነው፡፡ በዚህ መሰረት ጥናቱ የተጠኝ መምህራኑን የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና የክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበሩን እንዴትነት ከተመለከተ በኋላ በመካከላቸው ተዛምዶ መኖሩን መርምሯል፡፡ ምርምሩ የተከናወነው በድኅረ አወንታውያን የምርምር ቀመረ እሳቤና በመሰረተ ግንባታውያን የመማር ንድፈ ሀሳቦች ዝንቅ ማሕቀፍነት ነው፡፡ መነጸሪያው እስካሁን ድረስ የተሰነዘሩ ቋንቋን የመማር ንድፈ ሀሳቦች ዝንቅ ሲሆን የጥናቱ ሞዴል ለጥናቱ እንዲመች ተደርጎ የተቀናበረ ተግባ-ግብይታዊ የመማር ማስተማር ሂደት ማሕቀፍ ነው፡፡ ለጥናቱ ጥምር የምርምር ንድፍና ተዛምዷዊ የምርምር ስልት በጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ መረጃዎች በይሆንታዊና ኢይሆንታዊ የንሞና ዘዴዎች ከተመረጡ ተጠኝዎች በአጭር ጊዜ ምልከታ፣ በተመራማሪ እለታዊ ማስታወሻና በሰነድ ምርመራ የተሰበሰቡ ሲሆን የተተነተኑት በይዘት ትንታኔና በሰነድ ትንታኔ ነው፡፡ በዚህ መሰረት በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሂደት በመምህራኑ የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና በክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበሩ መካከል ጠንካራ አወንታዊ ተዛምዶ መኖሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የመምህራኑ የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምም ሆነ የክፍል ውስጥ መስተጋብሩ ከሚጠበቀው አንጻር ደካማ ናቸው፡፡ በተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምም ሆነ በክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበር ረገድ የትምህርት ደረጃቸው ዲግሪ የሆነ መምህራን የትምህርት ደረጃቸው ዲፕሎማ ከሆኑ መምህራን ተሽሎ የተገኘ ቢሆንም በሁለቱም የትምህርት ደረጃ ያሉ መምህራን የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና የክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበር ከሚጠበቀው አንጻር ደካማ ነው፡፡en_US
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/22034
dc.language.isoamen_US
dc.publisherAAUen_US
dc.subjectበአማርኛ ቋንቋ መምህራን የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምen_US
dc.titleበአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሂደት የመምህራኑ የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና የክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበሩ ተዛምዶ (የካ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ሶስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ የተደረገ ጥናት)en_US
dc.typeThesisen_US

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
መሰለ መግንቱ.pdf
Size:
3.5 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Plain Text
Description: