በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሂደት የመምህራኑ የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና የክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበሩ ተዛምዶ (የካ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ሶስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ የተደረገ ጥናት)

No Thumbnail Available

Date

2012-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

AAU

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና አላማ በአማርኛ ቋንቋ መምህራን የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና በክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበሩ መካከል ተዛምዶ መኖሩን መመርመር ነው፡፡ በዚህ መሰረት ጥናቱ የተጠኝ መምህራኑን የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና የክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበሩን እንዴትነት ከተመለከተ በኋላ በመካከላቸው ተዛምዶ መኖሩን መርምሯል፡፡ ምርምሩ የተከናወነው በድኅረ አወንታውያን የምርምር ቀመረ እሳቤና በመሰረተ ግንባታውያን የመማር ንድፈ ሀሳቦች ዝንቅ ማሕቀፍነት ነው፡፡ መነጸሪያው እስካሁን ድረስ የተሰነዘሩ ቋንቋን የመማር ንድፈ ሀሳቦች ዝንቅ ሲሆን የጥናቱ ሞዴል ለጥናቱ እንዲመች ተደርጎ የተቀናበረ ተግባ-ግብይታዊ የመማር ማስተማር ሂደት ማሕቀፍ ነው፡፡ ለጥናቱ ጥምር የምርምር ንድፍና ተዛምዷዊ የምርምር ስልት በጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ መረጃዎች በይሆንታዊና ኢይሆንታዊ የንሞና ዘዴዎች ከተመረጡ ተጠኝዎች በአጭር ጊዜ ምልከታ፣ በተመራማሪ እለታዊ ማስታወሻና በሰነድ ምርመራ የተሰበሰቡ ሲሆን የተተነተኑት በይዘት ትንታኔና በሰነድ ትንታኔ ነው፡፡ በዚህ መሰረት በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሂደት በመምህራኑ የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና በክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበሩ መካከል ጠንካራ አወንታዊ ተዛምዶ መኖሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የመምህራኑ የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምም ሆነ የክፍል ውስጥ መስተጋብሩ ከሚጠበቀው አንጻር ደካማ ናቸው፡፡ በተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምም ሆነ በክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበር ረገድ የትምህርት ደረጃቸው ዲግሪ የሆነ መምህራን የትምህርት ደረጃቸው ዲፕሎማ ከሆኑ መምህራን ተሽሎ የተገኘ ቢሆንም በሁለቱም የትምህርት ደረጃ ያሉ መምህራን የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀምና የክፍል ውስጥ መስተጋብር አተገባበር ከሚጠበቀው አንጻር ደካማ ነው፡፡

Description

Keywords

በአማርኛ ቋንቋ መምህራን የተግባቦት ክህሎት አጠቃቀም

Citation