የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች አጠቃቀም ከፆታ አንፃር፤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጋራ ጉሪ የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2022-01

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና አላማ የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች አጠቃቀም ከፆታ አንጻር ምን እንደሚመስል መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ሲሆን በጥናቱ የተሳተፉት በአላማ ተኮር ናሙና የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ብዛት ወንዶች 41 ሴቶች 40 ጠቅላላ 81 ናቸው፡፡ከተሳታፊዎች መረጃ የተሰበሰበው በሁለት የተለያዩ የመረጃ መሰብሰቢያ የፅሁፍ መጠይቅና የቃል መጠይቅ ናቸው፡፡ የፅሁፍ መጠይቁ አንብቦ የመረዳት ብልሃትን፣ ለመለካት ሲያገለግል ቃለ መጠይቁ ደግሞ ተጨማሪ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ በመሆን አገልግሏል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች በመቶኛ ስሌት ተሰልቶ በገላጭ ምርምር ዘዴ ተተንትነዋል፡፡ ስለሆነም አብይ ዓላማውን መሠረት በማድረግ ምርምሬ ከአነብቦ መረዳት ንዑስ ብልሃቶች ውስጥ የበለጠ የሚጠቀሙት የትኛውን እንደሆነ ለማወቅ በመቶኛ ስሌት ተሰልተው ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ለዚህም ተማሪዎቹ ስላላቸው የአንብቦ መረዳት አጠቃቀም ከሞሉት የፅሁፍ መጠይቅ የተገኘው መረጃ በአእምሯዊ፣ ትውስታ፣ አካካሽ፣ ልዕለ አእምሯዊና ማህበራዊ በሚሉ አምስት ንዑስ ብልሃቶች ጉልህ ሳይሆን ተቀራራቢ ሆኖ ተገኝቷል፡፡በተጨማሪነትየታየው ሌላኛው ዝርዝር ዓላማ በሴትና በወንድ ተማሪዎች ጉልህ የሆነ የአንብቦ መረዳት ብልሃት አጠቃቀም መኖር አለመኖሩን መፈተሽ ሲሆን በፍተሸው መሰረትም የተሰበሰቡን መረጃዎች በመቶኛ ስሌት በፍተሻው ስሌት ተሰልቶ ወንዶች 22.27 ሴቶች 18.75 በመሆኑ ወንዶች ከሴቶች የተሻለ አንብቦ የመረዳት አጠቃቀም መኖራቸውን ያመለክታል፡፡ በመጨረሻም የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግ አስተያየቶችተጠቁመዋል፡፡

Description

Keywords

የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች

Citation