በሰበታ መርሐ እውራን ልዩ ትምህርት ቤት የአማርኛ ቋንቋ የንባብ ትምህርት አተገባበር ፍተሻ (በ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተተኳሪነት)
No Thumbnail Available
Date
2010-06
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
Addis Ababa University
Abstract
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በሰበታ መርሐ እውራን ልዩ ትምህርት ቤት የአማርኛ ቋንቋ
የአንብቦ መረዳት ትምህርት ትግበራ ምን እንደሚመስልና የአይነስውር ተማሪዎችን
ልዩ ፍላጎትና ሁኔታ ከግምት ያስገባ መሆን አለመሆኑን መፈተሽ ነው፡፡ ከዚህ
አጠቃላይ ግብ ለመድረስ የአይነታዊ ምርምር ንድፍ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ
ተሳታፊዎችም የሰበታ መርሐ እውራን ልዩ ትምህርት ቤት የ2010 ዓ.ም የ7ኛ እና
8ኛ ክፍል አይነስውር ተማሪዎች እንዲሁም የአማርኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ
መምህራን ናቸው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በወሳኝ የናሙና አመራረጥ፣ በጠቅላይ
የናሙና አመራረጥ፣ በኮታ የናሙና አመራረጥ እንዲሁም በብድግ ብድግ የናሙና
አመራረጥ ስሌት ተመርጠዋል፡፡ ለመረጃ መሰብሰቢያ የተመረጡ መሳሪያዎች ደግሞ
የክፍል ውስጥ ምልከታ፣ የጽሁፍ መጠይቅ፣ ቃለመጠይቅና የተተኳሪ ቡድን ውይይት
ናቸው፡፡ የጥናቱ ግኝትም አጠቃላይ የመማሪያ ክፍል ሁኔታው የአይነስውር
ተማሪዎችን የንባብ ትምህርት ሂደት የሚደግፍ፣ አግባብነት ያለው፣ ተስማሚና ምቹ
እንደሆነ ታይቷል፡፡ የቅድመ ንባብ፣ የንባብ ጊዜ እና የድህረ ንባብ ትምህርት
ጊዜዎች በተለያዩ ተግባራት ታጅበው የሚከናወኑና በአብዛኛው በጥሩ ሁኔታ ላይ
የሚገኝ ቢሆንም፤ የአይነስውር ተማሪዎችን ልዩ ፍላጎት ከግምት ባስገባ መልኩ
አስማምቶና አጣጥሞ ማቅረብ ላይ፣ አይነስውር ተማሪዎቹን ማእከል ያደረገ በቂ
የንባብ ጊዜ ከመመደብ/ከመስጠት አንጻር እንዲሁም የአይነስውር ተማሪዎችን የንባብ
ትምህርት ለማጎልበት የሚረዱ ስልቶችንና ብልሀቶችን ከማስተዋወቅና
እንዲጠቀሙባቸው ከማበረታታትና ከማገዝ አኳያ ክፍተቶች ታይተዋል፡፡ እነዚህን
ክፍተቶች ለመድፈንና ለተሻለ የአይነስውራን የንባብ ትምህርት ሂደት ይረዳሉ
የተባሉ ሀሳቦችም ተሰንዝረዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የአንብቦ መረዳት ትምህርት
ስልቶችና ብልሀቶችን የሚያስተዋውቅና ከዘመኑ ጋር የሚሄድ ስልጠና ለአማርኛ
ቋንቋ መምህራን ማመቻቸት፣ የንባቡን ርእስ እና ይዘት ከተማሪዎች ልዩ ፍላጎትና
ሁኔታ ጋር አጣጥሞና አስማምቶ ማቅረብ እንዲሁም የአይነስውር ተማሪዎችን
አንብቦ መረዳት የሚያጎለብቱ እንደ ተዳሳሽ ቁስ፣ የድምጽ ግብአትና እውን ቁሶችን
ከንባብ ትምህርቱ ጋር በማዛመድ ተግባራዊ ማድረግ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
Description
Keywords
የአማርኛ ቋንቋ የአንብቦ መረዳት ትምህርት ትግበራ ምን እንደሚመስልና የአይነስውር ተማሪዎችን ልዩ ፍላጎትና ሁኔታ