የቃሊት ትምህርት አተገባበር ትንተና (በጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ በበህር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍል መምህራን ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

ይህ ጥናት የቃላት ትምህርት አተገባበር በተመለከተ በጉራጌ ዞን በቡታጀራ ከተማ በበህር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍልመምህራን ተተኳሪነት የተከናወነ ጥናታዊ ስራ ነው፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ ምርምር እና አሃዛዊ የምርምር ዘዴን የተከተሇ ሲሆን በቡታጅራ ከተማ በበህር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘጠነኛ ክፍል መምህራን የቃላት ትምህርት አተገባበር በተጨማሪ የቃላት ትምህርት አቀራረብ እና በቃላት ትምህርት የተማሪዎች ተሳትፍ በመፈተሽ ትንትና ተደርጓል፡፡ በዚህ ጥናት የተካተቱ መምህራን ቃላትን እንዴት እንደሚያቀርቡ፤ በመማር ማስተማር ሂደት ቃላትን እንዴት እንደሚተገብሩ እና ተማሪዎች ቃላትን በመማር ሂደት ያላቸውን ተሳትፎለመመልከት መረጃዎችን ከመምህራን እና ከተማሪዎች እንዲሰበሰቡ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት የክፍል ውስጥ ምልከታ እና የጽሐፍ መጠይቆች በመረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያነት ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች በተገኘ መረጃ መሰረት የቃላት ማስተማሪያ መንገዶች መካከልቃሊትን በተመሣሣይ እና በተቃራኒ ፍቻቸው ማቅረብ፤ ቃላትን በአውድ ማቅረብ እና ቃላትን ከክሂሎች ጋር በማጣመር ከማቅረብ አንፃር መምህራን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚተገብሯቸው፤ በአንጻሩም የቃላዊ ሀረጎችን ለመረዲትና ለማፍለቅ በሚያስችል ስልት ማቅረብ፣ ቃላትን አካታችና ተከታች ግንኙነት መሰረት አድርጎ ማቅረብ እና ቃላትን ምንባብ በማዘጋጀት ከማቅረብ አንፃር ዝቅተኛ በሆነ ደረጃ እደሚጠቀሙባቸው ጥናቱ አመልክቷል። የመማሪያ መጽሐፌፍ እጥረት፣ የተማሪ መብዛት፣ የክፍለጊዜ መደራረብ፣ የቃላት ትምህርት የማስተማሪያ መንገድችን አለመተግበር፣ ቃላትን የማስተማሪያ መርለችን ያለመከተል፣ መረበሽ፣ የተማሪዎች ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑ እና ለቋንቋው የተሰጠው ክፍለጊዛዜ ማነስ የመሳሰለ ችግሮች ለቃላት ትምህርት አተገባበር ተግዳሮት መሆናቸው ጥናቱ አመላክቷል፡፡

Description

Keywords

የቃላት ትምህርት አተገባበር

Citation