የሰብዓዊነት መንጠፍ ኪናዊ ፈርጆችና ረቦች በየሕሊና ባርነት ልቦለድ ውስጥ
dc.contributor.advisor | ገብሬ, ቴዎድሮስ (ፕሮፌሰር) | |
dc.contributor.author | ሽመልስ, ወንድወሰን | |
dc.date.accessioned | 2019-02-08T06:38:47Z | |
dc.date.accessioned | 2023-11-09T04:06:50Z | |
dc.date.available | 2019-02-08T06:38:47Z | |
dc.date.available | 2023-11-09T04:06:50Z | |
dc.date.issued | 2010-06 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት “የሰብዓዊነት መንጠፍ ኪናዊ ፈርጆችና ረቦች በየሕሊና ባርነት ልቦለድ ውስጥ” በሚል ርዕስ የተከናወነ ሲሆን፤ በልቦለዱ ውስጥ የሰብዓዊነት መንጠፍ እንዴት ቀረበ የሚለውን የማሳየት ዓላማን ይዟል፡፡ ንድፈ ሀሳባዊ ዳራውም የሞራል ፍልስፍና (የግብረ ገብ እሴቶች አንጻር) ሲሆን፤ በአውዱ (ቴክስቱ) መሰረትነት የሰብዓዊነት መንጠፍ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ በዚህም መሰረት ጥናቱ በልቦለዱ የሰብዓዊነት መንጠፍ መከሰቻ ኪናዊ ፈርጆች ምን እንደሆኑ በመለየት ኪኖቹ የሚኖራቸውን ረብ ለመመርመር ሞክሯል፡፡ ጥናቱ በትንታኔው ለሰብዓዊነት መንጠፍ ምክንያት ከሆኑ እስቦችና ክዋኔዎች (ከሃሳብ እስከ ተግባር የሚገለጹትን ለማለት ነው) በልቦለዱ ውስጥ ለሰብዓዊነት መንጠፍ መሄሻነት እንዴት እንደተከሰቱ እና የቀረቡበት አግባብ የደራሲውን ርዕይ ከማሳየት አኳያ ያላቸው ረብ በጽንሰ ሃሳብ መተንተኛነት ከየታሪኮቹ በሚወሰዱ አስረጂዎች አማካኝነት አቅርቧል፡፡ በዚህም የልቦለዱ ታሪክ ፊት ለፊት ይዞ ከቀረበውና እንደ ሰም ማልበሻ ሆነው ከሚያገለግሉት ውቅሮች ባሻገር፤ ልቦለዱ ሲመረመር ሰው እንደ ሰው አካል ገዝፎ እየታየ ነገር ግን የሰውነት ባህሪን ሲያጣ፣ ግብረገባዊ እሴቱ ሲከስም፣ በአጠቃላይ የሰውነት መገለጫዎቹ ሲነጥፉበት ይታያል፡፡ በልቦለዱ የሰብዓዊነት መንጠፍ በዋናነት በሁለት መልኩ የተከሰተ ሲሆን፤ አንዱ የሰው ልጅ ሰዋዊ ባህርይና ምግባሩን ትቶ ከእንስሳት ጎራ ተቀላቅሎና በዚሁ ተገልጾ የታየበት የ“አኒማሊስቲክ ዲሂዩማናይዛሽን” ፈርጅ ነው፡፡ ሁለተኛውም ደግሞ የሰው ልጅ ከሰውነት ሚዛን ወርዶ በቁስ ሚዛን የተለካበትና እንደ እቃ የተቆጠረበት የ“ሜካኒስቲክ ዲሂዩማናይዜሽ” ፈርጅ ነው፡፡ በመሆኑም በጥናቱ፣ በልቦለዱ ውስጥ የሰው ልጆች የግብረ ገብ (ሞራል) እሴቶቻቸውን ቸል ብለው፣ ስብዕናቸውን ረስተው፣ ራስ ወዳድነትን አንግሰውና አብሮነትን ዘንግተው ራሳቸውን ከእንስሳት ጎራ አስመድበው፤ ከቁስ ተርታም ተሰልፈው በዛው መጠን አንዱ ሌላኛውን የገለጸበትን ሂደት ለመመርመር ጥረት አድርጓል፡፡ | en_US |
dc.identifier.uri | http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/16314 | |
dc.language.iso | en | en_US |
dc.publisher | Addis Ababa University | en_US |
dc.subject | “የሰብዓዊነት መንጠፍ ኪናዊ ፈርጆችና ረቦች በየሕሊና ባርነት ልቦለድ ውስጥ” | en_US |
dc.title | የሰብዓዊነት መንጠፍ ኪናዊ ፈርጆችና ረቦች በየሕሊና ባርነት ልቦለድ ውስጥ | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |