በየካቲት 12 የመሰናዶ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ትምህርት ነክ ያልሆኑ ጽሁፎችን የማንበብ ልምድ

dc.contributor.advisorአስማረ, ተሻገር
dc.contributor.authorገ/ኪዳን, አቤል ገ/ኪዳን
dc.date.accessioned2018-06-13T10:11:53Z
dc.date.accessioned2023-11-09T04:05:46Z
dc.date.available2018-06-13T10:11:53Z
dc.date.available2023-11-09T04:05:46Z
dc.date.issued2001-06
dc.description.abstractየዚህ ጥናት ዋና አላማ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎችን ትምህርት ነክ ያልሆኑ ጽሁፎችን የማንበብ ልምድ መመዘን ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ት/ቢሮ የጉለሌ ክ/ከ ት/መምሪያ ስር በሚገኘው የየካቲት 12 የመሰናዶ ት/ቤት ነው፡፡ መረጃዎችም ከመምህራን እና ከተማሪዎች በመጠይቅ አማካኝነት ተሰብስበዋል፡፡ ት/ቤቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተማሪ የሚያስተናግድ ሲሆን ሁሉንም ተማሪዎች መመዘን ስለማይቻል ከ11ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 80 ተማሪዎች በመጠይቁ ውስጥ ተካተዋል፡፡ የእነዚህን ተማሪዎች ምላሽ ለማረጋገጥም በት/ቤቱ የሚያስተምሩ 6 የቋንቋ መምህራን በመጠይቅ መረጃ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ የተገኘው ውጤትም ተተንትኗል፡፡ በጥናቱ የተገኘው ውጤትም የሚያመለክተው የተማሪዎች ትምህርት ነክ ያልሆኑ ጽሁፎች የማንበብ ልምድ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ተማሪዎች ስለ ንባብ ያላቸው ግንዛቤ እጅግ ዝቅተኛ መሆን፣ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ጫና፣ የትምህርት ቤቶች ንባብን በማስለመድ ረገድ ሊኖራቸው የሚገባ አስተዋጽኦ በሚገባ መወጣት አለመቻል ናቸው፡፡ ስለዚህም ወደፊት ትምህርት ነክ ያልሆኑ ጽሁፎችን የማንበብ ልምድ ለማዳበር ሊደረጉ ይገባቸዋል ብሎ አጥኚው የተወሰኑ ሀሳቦችን ሰንዝሯል፡፡ እነሱም የንባብ ክፍል ማዘጋጀት፣ ከፍተኛ ቅስቀሳ ማካሄድ እና ሳቢነት ያላቸውን ጽሁፎች በመማሪያ መጻህፍት ውስጥ ማካተት ናቸው፡፡en_US
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/691
dc.language.isoamen_US
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲen_US
dc.subjectየመሰናዶ ትምህርት ቤትen_US
dc.titleበየካቲት 12 የመሰናዶ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ትምህርት ነክ ያልሆኑ ጽሁፎችን የማንበብ ልምድen_US
dc.typeThesisen_US

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
አቤል ገኪዳን.pdf
Size:
678.4 KB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Plain Text
Description: