በመደበኛው እና በማታው መርሃ ግብር የሚያስተምሩ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የማንበብ ክሂል ትምህርት የክፍል ውስጥ አተገባበር ንጽጽራዊ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተመረጡ የመንግስት ትምህርት ቤቶች (በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ

Abstract

የዚህ ጥናት አብይ አላማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች በመደበኛው እና በማታው መርሃ ግብር የሚያስተምሩ መምህራን የማንበብ ክሂል ትምህርት የክፍል ውስጥ አተገባበር ምን እንደሚመስል በንጽጽር መፈተሽ ነው፡፡ ይህንም አላማ ከግብ ለማድረስ አጥኚዋ የተጠቀመችው ቅይጥ የምርምር ዘዴን ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደባቸው ትምህርት ቤቶችም ላፍቶ 2ኛ ደረጃና ለቡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ፣ የተመረጡትም በአመቺ የናሙና ዘዴ ነው፡፡ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች በመደበኛው መርሃ ግብር የሚያስተምሩ አራት እንዱሁም በማታው መርሃ ግብር የሚያስተምሩ አራት በድምሩ ስምንት መምህራንን በጠቅላይ የንሞና ዘዴ በመምረጥ በእያንዳንዱ መምህር ሶስት ሶስት ጊዜ በድምሩ ለሃያ አራት ጊዜ የክፍል ምልከታ በማድረግ በተጨማሪም ለመምህራኑ ቃለመጠይቅ በማቅረብና ተማሪዎችን የጽሐፍ መጠይቅ በማስሞላት ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ እነዚህ መረጃዎችም በገለፃና በቁጥር የመረጃ መተንተኛ ዘዴዎችን በቅንጅት በመጠቀም በንጽጽር ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ ከትንተናው የተገኘው ውጤትም የሚያመለክተው መምህራኑ የማንበብ ክሂል ትምህርትን በሚያስተምሩበት ወቅት በአብዛኛው የሚከተለት የጮክታ ንባብ መሆኑ፤ በንባብ ክሂል ትምህርቱ አተገባበር የመደበኛው መርሃ ግብር መምህራን ከማታው መርሃ ግብር መምህራን የተሻለ መሆናቸው፤ እንዱሁም ለማታው መርሃ ግብር የተመደበው ክፍለጊዜ ዝቅተኛ መሆን የማንበብ ክሂል ተግባራቱን በአግባቡ ለመተግበር እንቅፋት መሆኑን የጥናቱ ውጤት ያመለክታል፡፡ የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግም መምህራን ውጤታማ የሆነ የማንበብ ክሂል ትምህርትን ለማስተማር የሚረደ የማንበብ ክሂል ተግባራትን በአግባቡ ቢተገብሩ፤ በመማሪያ መጻህፍት ውስጥ ካለ ምንባቦች በተጨማሪ የተለያዩ የስነ-ጽሐፍ ውጤቶችን እያቀረቡ ቢያስተምሩ፣ የትምህርትቤቶቹ አስተዳደር ተማሪዎቹም ሆነ መምህራን ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ የተለያዩ የስነ-ጽሐፍ ምንጮችን በትምህርት ቤቱ ቤተ-መጻህፍት ውስጥ ተሟልተው እንዲቀርቡ ቢደረግ የሚሉ አስተያየቶች ተጠቁመዋል፡፡

Description

Keywords

የዚህ ጥናት አብይ አላማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች

Citation