በሲዳምኛ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የማርኛ ቃላት ሲማሩ የሚጠቀሙባቸውን ቃላትን የመማር ብቃቶች ምርመራ
No Thumbnail Available
Date
2000-06
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በሲዳምኛ አፋቸውን የፈቱ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ ቃላትን የመማር ብልሃቶች
መመርመር ነው ጥናቱ ሲዳማ ዞን ውስጥ መሰናዶ ትመህርት (11ኛ እና 12ኛ) ክሚሰጥባቸው አራተ የመንግስት
ትምህርት ቤቶች መካክል በቀላል የእጣ ናሙና ዘዴ በተመረጡ ሁልት ትምህርተ ቤቶች (በአዋሳ ታቦርና በይርጋልም)
በ11ኛ ክፍል የሚማሩ በሲዳምኛ አፋቸውን የፈቱ 80 ተማሪዎችን በተመጣጣኝ ናሙና ዘዴ በመውሰድ በአይነታዊ
የምርምር ዘዴ ያካሄደ ግልጭ ጥናት ፡፡ በዜህም መሰርት የሁልትኛን ቀንቃ ቃላት በቀላሉ ለመማር በተለያየ መንገድ
እገዛ በሚያደርጉ መንግድ የትውስታ አውታራዊ ስሜት ነኪ ቁጥጥር እና ማህብራዊ ብልሃቶች ስር በተካተቱ
ዝርዝር ብልሃቶች ላይ በማተኮር ተጠኚ ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ ቃላትን ሲማሩ የተጠቀሱትን የመማር ብልሃቶች
ምን ያህል እንደሚገለገሉባቸው ለመፈተሽ ተሞክሯል ፡፡
ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በጹሑፍ መጠየቅና በቃለ መጠይቅ የተስበሰቡ ሲሆን በጹሑፍ መረጃዎችም
በስድስት ንኡሳን የመማር ብልሃቶች ስር በሠንጠረዥ ተደራጅተው በቁጥርና በመቶኛ ተጠቃልለው እንዲታዩ
በማድረግ በቃለ መጠይቅ ከተገኙ መረጃዎች እየተደጋገፍ ተተንትነዋል፡፡
በሁልቱም የመረጃ መሰብሰቢያ መሳርዎች በተገኙ መረጃዎች ትንተና ትንተና ውጢት መሰረት ተማሪዎቹ
የአማርኛ ቃላትን በቀላሉ ለመማር በተለያየ መንገድ እገዛ የምያደርጉ ቃአላትን የመማር ብልሀቶች በቃላት በመጠቀም
ላይ የተመሰረተ ሆኖ አልተገኝም ፡፡አብዛኛው ተማሪዎች የታላሚውን ቋንቋ አዳዲስ ቃላት በአምሮአቸው መዝግበው
የረጅም ጊዜ ትውስታ ለመፍጠር የሚያግዛቸውን የትውስታ ብልሃቶች በትምህረቱ ሂደት የሚሰማቸውን የረፍርሃት
የጭንቀት አሉታዊ አመለካከትና ዝንባሌ ለመቆጣጠር የሚረዳቸውን ስሜት ነኪ ቁጥጥር ብልሃቶችን ለማዳበር
በሚል አላማ ከክፍል ጓደኛቻቸው ጋር እየተረዳዱ መምህሮቻቸውን እየጠየቁ የመማር ማህበራዊ ብልሃቶችንና
ለቃላት ትምህርት የክንውን አቅድ በማዘጋጀት አላማና ግብ በመንደእፍ ስተታቸውን በራሳቸው በመለየትና
በመገምገም እንዲማሩ የሚያግዛቸውን ልእለ አምሮታዊ ብልሀቶችን አብዛኛዎች ተማሪዎች ተማሪዎች
አልፎ አልፎ እደሚገለገሉባቸው የተገኝ መረጃ ትንተና ውጤት ያመለክታል፡፡