የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች የክፍል ውስጥ አተገባበርን በንፅፅር መፈ ተሸ፤ (በአዲስ አበባ በተመረጡ ሁለት የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ው ስጥ የሚያስተምሩ የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ተተኳሪነት)
No Thumbnail Available
Date
2023-10
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
ይህ ጥናት የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች የክፍል ውስጥ አተገባበርን በንፅፅር ፈትሿል፡ጥናቱም አወዳዳሪ የምርምር ንድፍን ተከትሏል፡፡በተጨማሪም ጥናቱ የተካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ካሉ የግልና የመንግስት ትምህርተ ቤቶች ውስጥ አመቺ የናሙና ዘዴን በመጠቀም ከግል ሆሉሲቨር ትምህርት ቤት ከመንግስት የብርሃነ ኀሊና ትምህርት ቤቶች በጥናቱ ተካተዋል፡፡ በዚህ ጥናት በመረጃ ሰጪነት የተሳተፉት በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ የስምንተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ወንድ 2 ሴት 2 በድምሩ 4 መምህራን ሲሆኑ እነዚህም በጠቅላይ ናሙና ተመርጠዋል፡፡ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ትምህርት ቤት 36 ተማሪዎች በቀላል የእጣ ናሙና ዘዴ ተመርጠው በጥናቱ ተካተዋል፡፡ በመጨረሻ በቁጥር መልክ የተሰበሰበውን መረጃ ገላጭ ስታትሰቲክስ (በአማካይ፣ መደበኛ ልይይትና በቲ-ቴስት ስታትሰቲክስ የመተንተኛ ስሌት) በመጠቀም ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ ግኝቶች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡ የግልም ሆነየመንግስትትምህርት ቤት መምህራን የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች አተገባበር ዝቅተኛና መሻሻል የሚ ገባው እንደሆነ አመላክቷል፡፡ ከሁለቱ የጥናቱ ተተኳሪትምህርት ቤቶች መካከል ግን የግል ትምህርት ቤት መምህራን ከመንግስት ትምህርት ቤት መምህራን የተሻለ የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች አተገባበር እንዳላቸው በጥናቱ ውጤት ተረጋግጧል፡ ፡ ይህም የመንግስት ትምህርት ቤት መምህራን የአንብቦ መረዳት ብልሃቶችን ለመተግበር በክፍል ውስጥ የተማሪ ቁጥር መብዛት እና የተማሪዎች መጽሐፍ ግብአት አለመሟላት፤ ወዘተ . ምክንያት የመነጨ እንደሆነ ከተካሄደው ቃለ መጠይቅ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በመጨረሻምጥናቱ ለችግሮች የመፍትሄ ሃሳቦችን በማቅረብ ተጠቃሏል፡፡
Description
Keywords
የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች