የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተማሪዎቻቸው የጽሁፍ መለማመጃ ላይ የሚሰጡት ፅሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ ፍተሻ በየካቲት 23 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2006-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

የጥናቱ ዓላማ የቋንቋ መምህራን በተማሪዎቻቸው የጽሁፍ መልመጃዎች ላይ የሚሰጧቸውን ጽሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ መፈተሽ ነው፡፡ አይነታዊና መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም ጽሁፋዊ ምጋቤ ምላሹ ተፈትሿል፡፡ ተጠኝዎች በየካቲት 23 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2006 ዓ.ም በ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋን በማስተማር ላይ ካሉ መምህራን ውስጥ በቀላል የዕጣ ንሞና ዘዴ አራት መምህራን ተመርጠዋል፡፡ ለጥናቱ በመረጃነት ያገለገሉት በመምህራን ታርመው የተመለሱ የተማሪዎች የፅሁፍ መልመጃዎች፣ የፅሁፍ መጠይቅና ቃለ መጠይቅ ናቸው፡፡ በመምህራን ፅሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ ተሰጥቶባቸው የተመለሱ የተማሪዎች ፅሁፎች ከምጋቤ ምላሽ አይነቶች ፣ከምጋቤ ምላሽ አሰጣጥ ስልቶች ፣ከምጋቤ ምላሽ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ ከምጋቤ ምላሽ መገለጫ ባህሪያት እና መስጫ ቦታዎች አንፃር ተተንትነዋል፡፡ በእነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች እያንዳንዳቸው መምህራን በተማሪዎች የፅሑፍ ወረቀት ላይ አብዛኛውን ጊዜ ትኩረት ያደረጉበትን የምጋቤ ምላሽ ዓይነት፣ የምጋቤ ምላሽ ስልትን፣ የምጋቤ ምላሽ ትኩረትን እና ባህሪን እንዲሁም መስጫ ቦታን ለመለየት ተችሏል፡፡ በመረጃ ትንተናው መሰረትም መምህራን ገምጋሚ ምጋቤ ምላሽን አዘውትረው እንደሚጠቀሙና በዋናነት ስህተቶችን መርጦ የማረም ስልትን ተጠቅመው የተማሪዎችን ፅሑፍ እንደሚያርሙ የትንተናው ውጤት አሳይቷል፡፡ እንዲሁም መምህራን በጽሁፉ ይዘትና ቅርጽ ላይ ትኩረት አድርገው ምጋቤ ምላሽ እንደሚሰጡ፣ አሉታዊነት የተላበሰ ምጋቤ ምላሽ እንደሚያበዙና በተማሪዎች ወረቀት ግራና ቀኝ ባሉ ቦታዎች ላይ በዋናነት ምጋቤ ምላሽ እንደሚሰጡ ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም መምህራን ግልጽና ከትምህርቱ አላማና ግብ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ምጋቤ ምላሽ እንደሚሰጡ፣ እንዲሁም ጽሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ የሰጡበትን የተማሪዎች የጽሁፍ ወረቀት ሆነ ደብተር በጊዜ እንደሚመልሱ በትንተናው ውጤት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ነገር ግን መምህራን ወጥ የሆነ ምጋቤ ምላሽ አይነት፣ ባህሪና መስጫ ቦታን ከሚያዘወትሩ እንደያስፈላጊነታቸው አየቀላቀሉ ምጋቤ ምላሽ ቢሰጡ አንድም ምጋቤ ምላሹ ውጤታማ ይሆናል፤የተማሪዎች የመጻፍ ክሂልም ይዳብራል፡፡

Description

Keywords

መለማመጃ ላይ የሚሰጡት ፅሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ ፍተሻ

Citation