አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ የሚማሩ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የቀረቡ የማዳመጥ ክሂል ትምህርት ክንውኖች የክፍል ውስጥ አተገባበር ግምገማ ፤በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ አርጊቲ ደነባ አንደኛ ደረጃ 2ኛ እርከን ትምህርት ቤት

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

ይህ ጥናት በዋናነት አላማ ያደረገዉ አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ የሚማሩ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የማዳመጥ ክሂል ትምህርት የክፍል ዉስጥ አተገባበር ግምግማ ላይ ሲሆን ተጠኚዎቹ በአመችነት የናሙና አመራረጥ የተመረጡና ገላጭ የትንተና ዘዴን የተከተለ ጥናት ነዉ፡፡ ጥናቱም የተከናወነው በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ አርጊቲ ደነባ አንደኛ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ኢ-አፍፈት የሆኑ 75 በተመረጡ ተጠኚ ተማሪዎች ላይ ነዉ፡፡ አጥኚዋ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በጽሁፍ መጠይቅ፣ በቃል መጠይቅና የክፍል ዉስጥ ምልከታ በማድረግ ሰብስባለች፡፡ በጽሁፍ መጠይቅና በቃለ መጠይቅ እንዲሁም በምልከታ በተገኘዉ ምላሽ በቅድመ ማዳመጥ ፣በማዳመጥ ጊዜ እና በድህረ ማዳመጥ ጊዜ ክፍል ዉስጥ አተገባበር ምን እንደሚመስል የመጠይቆቹን ጥያቄዎች በሰንጠረዥ ዉስጥ በቁጥርና በመቶኛ እንዲሁም በገለጻ ተተንትኗል፡፡ በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች አማካይነት በተገኙ የመረጃዎች ትንተና ዉጤት መሰረት ተጠኚ ተማሪዎች የማዳመጥ ክሂል ትምህርት በክፍል ዉስጥ ሲተገበር የተገኘው ምላሽ እንደማይተገበርና ቢተገበርም አተገባበሩም ደካማ መሆኑ ከጥናቱ የተገኘዉ ዉጤት ያሳያል፡፡ ከተጠኚ መምህራን የተገኘ ምላሽም የማዳመጥ ክሂል ይዘቶችን በክፍል ዉስጥ የሚተገብሩት አልፎ አልፎ እንደሆነ በጥናቱ ዉጤት ታዉቋል፡፡ ሌላዉ መምህራን ከተማሪዎቹ ችሎታ፣ ዳራና ፍላጎት ጋር የሚጣጣሙ ይዘቶችን በማዘጋጀት እንደማያቀርቡ በጥናቱ ዉጤት ዉስጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንዲሁም ተጠኚዎቹ ክሂሉን ለማዳበር ይችሉ ዘንድመምህራን ክሂሉን ሲተገብሩ የተለያዩ ስልቶችን ለምሳሌ የተቀረጹ ድምጾችን፣ አጫጭር ታሪኮችንና ሥነጽሁፋዊ ስራዎችን ወደ ክፍል ዉስጥ በማምጣት እንደማያስደምጧቸዉና በዚህም ምክንያት ዉጤታማነቱ ዝቅተኛ መሆኑን አጥኚዋ ተገንዝባለች፡፡ ከዚም በተጨማሪ የማዳመጥ ክሂል ትምህርት አተገባበር ላይ ትልቅ ተግዳሮት የሆነና ተጠኚ መምህራንም የገለጹት ጉዳይ፡- ተጠኚዎቹም ሆኑ ተማሪዎች ቋንቋዉን የሚማሩት እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ስለሆነ ተጠኚዎቹ ከወዲሁ የቋንቋዉ ትምህርት ይከብዳል፣ አይገባኝም በማለት እና ለቋንቋዉ ትምህርት ያላቸዉ ፍላጎት አናሳበመሆኑ ከየት መጣ የክሂሉን እዉቀት በታሰበዉ ልክ መተግበር አለመቻላቸዉን በጥናቱ ዉስጥ ተጠቅሷል፡፡ ሌላዉ ጉዳይ ለቋንቋዉ መምህራን ለክሂሉ መዳበርም ሆነ ለቋንቋዉ ትምህርት ዉጤታማነት አጫጭር ስልጠናና ዎርክ ሾፖች ስለማይሰጣቸዉ በክሂሉ አተገባባር ላይ ተጽእኖ እነዳሳደረባቸዉ በጥናቱ ዉስጥ ተረጋግጧል፡፡

Description

Keywords

የማዳመጥ ክሂል፡አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ የሚማሩ

Citation