የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲዳምኛ የሆኑ የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸው አመለካከትና ውጤት ተዛምዶ (በሀዋሳ ምስራቅ ጮራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የሀዋሳ ምስራቅ ጮራ ት/ቤት ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸው አመለካከት ከአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ውጤት ጋር ያለውን ተዛምዶ መፈተሸ ሲሆን ጥናቱ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ተዛምዷዊ የምርምር ንድፍን የተከተለ ነው ፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት ይረዳ ዘንድ በ2015 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምስራቅ ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 10ኛ ክፍል ከሚማሩና አፍ መፍቻቸው ሲዳምኛ ከሆኑ 295 ተማሪዎች 35% በመውሰድ በአጠቃላይ 103 ተማሪዎች በእኩል ዕድል ሰጪ የናሙና አመራረጥ ስልት በተጠኚነት ተመርጠዋል፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች የጽሁፍ መጠይቅና የሰነድ ፍተሻ ነው፡፡ የመረጃ መተንተኛዎቹም የተዛማች ስሌትና የአስተማማኝነት ግንኙነት መለኪያ ስልቶች ናቸው፡፡የተማሪዎች አጠቃላይ አመለካካት አማካይና የአንደኛ ወሰነ ትምህርት በክፍል መምህራን የተሰጡ የአማርኛ ፈተናዎች አማካይ ውጤት ያለው ተዛምዶ በፒርሰን የተዛምዶ መለኪያ ቀመር መሰረት በኮምፒዩተር ኤስ ፒ ኤስ ኤስ ተሰልቶ ቀርቧል ፡፡ ስሌቱም ያሳየው በአመለካከትና በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ውጤት መካከል አዎንታዊ የሆነ ተዛምዶ መኖሩን ነው፡፡ የሁለቱ ተላውጦዎች ዝምድና መጠን መካከለኛ (0.456) መሆኑን የተገኘው ውጤት አረጋግጧል ፡፡ በዚሁ መሰረት ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸው መለካከትና በፈተና ውጤታቸው መካከል መካከለኛ ተዛምዶ መኖሩንና ይህ ዝምድና ከፆታ አንፃር ልዩነት ይኖረው እንደሆነ በዚሁ በፒርሰን ተዛምዶ ተሰልቶ መጠኑ የተገለፀ ሲሆን ውጤቱ ያመላከተው ከፆታ አንፃር ልዩነት የሌለው መሆኑን ነው ፡፡ ስለሆነም የተማሪዎች ውጤት ማነስ ከአመለካከት ጋር የተያያዘ በመሆኑ በአመለካከት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የጥናቱ ውጤት ያመላክታል፡፡

Description

Keywords

አማርኛ ቋንቋ ትምህርት

Citation