በሲዳማ ክልል ከ2013 እስከ 2014 ዓ/ም የተዘጋጁ የስምንተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ
No Thumbnail Available
Date
2022
Authors
እናኑ ተስፋዬ
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በሲዳማ ክልል ከ2013 እስከ 2014 ዓ/ም የተዘጋጁ የስምንተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻላይ ነው፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሳካት ሰነድ ፍተሻበመረጃ መሰብሰቢያነት አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ የጥናቱ ናሙናዎች ወይም የክልልና የፈተናዎች አመራረጥ የተመረጡት በአመቺ ንሙና ዘዴ ሲሆን የተመረጡት የመረጃ ምንጮች በ2013 ዓ/ም እና 2014 ዓ/ም ለ8ኛ ክፍል የተሰጡ ክልል አቀፍ ፈተናዎች በዐብይ የመረጃ ምንጭነት ሲያገለግሉ በአጋዥነትደግሞየ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል መርሀ ትምህርቶች ናቸው፡፡ ከዚህ የመረጃ ምንጮች የተሰበሰቡት መረጃዎች አይነታዊን በዋናነት መጠናዊን በአጋዥነት በመጠቀም ትንተናው ተከናውኗል፡፡ የመርሀ ትምህርቶችን ተዛምዶ ለመፈተሸ መረጃዎችን በቁጥርና በመቶኛ በማስላት በገለፃ ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ የፈተናዎች የይዘት ተገቢነት በተመለከተ በገላጭ አይነታዊአተናተን ስልት በመጠቀም በፈተናው ውስጥ የቀረቡትን 120 ጥያቄዎች በመፈተሸ የሚታይባቸውን ጠንካራና ደካማ ጎን በማውጣት ትንተናው ተካሂዷል፡፡ በትንተናውም የተገኙት ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ፈተናዎችሁ ከመርሀ ትምህርቶች ጋር ያላቸውን ዝምድና በሚመለከት በሁለቱም ዓመተምህረቶች የቀረቡትንየፈተናጥያቄዎችመርሃ ትምህርትን ሽፋን ከማዳረስአንፃር ተመጣጣኝ አይሁን እንጂ በሁሉም ክሂሎችና የዕውቀት ዘርፎች መርሀ ትምህርቱን ለማዳረስ ጥረት ተደርጓል፡፡ የመናገርናየማዳመጥ ክሂል ፈተና ከመርሃ ትምህርቱ አንፃር ተደራሽነቱ ውስን ነው በመሆኑም የመርሀ ትምህርትን ሽፋንከመጠበቅ አንፃር የጥያቄዎቹ ፍትሀዊነት ወይም ተደራሽነት ጉድለት ተስተውለዋል፡፡ እነኚህ ችግሮች ወደፊትመስተካከል ቢቻል የተሸለ እንደሚሆን በአስተያየት ላይ ተጠቁሟል፡፡
Description
Keywords
የስምንተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች