የታች-ላይ (Bottom up) የንባብ ማስተማሪያ ሞዴል በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ክህልን ለማዳበር ያለው ውጤታማነትና ተተግባሪነት፤ (አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት በሚማሩ በዘጠነኛ ከፍል ተማሪዎች ላይ የተካሄደ ጥናት፡፡)
No Thumbnail Available
Date
2023-09
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ርዕስ “የታች ላይ/Bottom Up/የንባብ ሞዴል አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳትን ክሂላቸዉን ከማጎልበት አንፃር ያለዉ ዉጤታማነትና ተተግባሪነት”የሚል ሲሆን ዋነኛ አላማ ያደረገዉም ይሄዉ የታች ላይ /Bottom Up/የንባብ ሞዳል አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ክህላቸዉን ከማጎልበት አንፃር ያለዉ ዉጤታማነትና ተተግባሪነት ምን ያህሌ እንደሆነ መመርመር ነዉ፡፡ ይህንንም አላማ ከግቡ ለማድረስ አጥኝዋ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን በሆሮ ቡልቅ ወረዲ በሠቀላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎችን መርጣለች፡፡ አመራረጡም ካሉት ትምህርት ቤቶች ይህ ትምህርት ቤት ብቻ አማርኛ ቋንቋን ስለሚማሩ ተጠኚዎቹም የቁጥጥር ቡድን እና የሙከራ ቡድን በሚል በዕጣ ናሙና የተከፈለ ሲሆን የተመረጡትም የ2015 የትምህርት ዓመት የ9ነኛ ክፍል ከየክፍሉ አምስት አምስት ተማሪዎችን በመዉሰድ ቡድን “ሀ” እና ቡድን “ለ”ብላ የመደበቻቸዉን ተማሪዎች ነዉ፡፡ ይህ ጥናት ዓይነቱ ሙከራዊ (Expermental)ጥናት ሲሆን በመረጃ መተንተኛነት በዋነኝነት የተከተለዉ ዘዴም መጠናዊ የምርምር ዘዴ ነዉ፤ በዚህም የሁለቱም ተጠኚ ቡዴኖች በቅድመና በድህረ ልምምድ ዉጤት ፌትነታዊ በሆነ መልኩ በመመርመር ዉሳኔ ላይ ለመድረስ ያለመ ነበር፡፡ በተጨማሪም በመረጃ መሰብሰቢያነት እንዲያገለግል የፅሐፍ መጠይቅና በባልደረባ እርዲታ ምክንያት ስያስተምሩ አጥኝዋ ተሳታፉ የሆነችበት የክፍል ምልከታ ማሰታወሻ መያዝ መሣሪያነት ተመርጠዉ ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ በዚሁም መንገድም መረጃዉ ተሰብስቦ ዉጤቱ ተተንትኗል፡፡ በጥናቱ የተደረሰበት መደምደሚያ እንደሚያመለክተዉ የታች ላይ የንባብ ማሰተማሪያ ሞዳልን በመጠቀም በተለይ አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት ለሚማሩ ተማሪዎች የምንባብ ትምህርትን ማቅረብ የተማሪዎችን አንብቦ የመረዲት ክሂል ከማዲበር አንፃር ጠቀሜታ እንዲለዉ መረዳት ተችሎዋል፡፡
Description
Keywords
አንብቦ የመረዳት ክህሎት፡