በአፋርኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች በአማርኛ ድርሰት ሲጽፉ የሚፈጽሟቸው የስህተት አይነቶች እና የስህተት ምንጮች ትንተና (በአፋር ክልል በዱብቲ እና ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-07

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በአፋር ክልል ዱብቲና ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአፋርኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ድረሰት በሚፅፉበት ጊዜ ከፅሁፎቻቸው ውስጥ ስህተቶችን እና የስህተት ምንጮች ተለይተዋል፡፡ በጥናቱ የተካተቱት ተማሪዎች የተመረጡትም ከእድል ሰጭ የንሞና አመራራጥ ዘዴ መካካል በቀላል የእጣ ንሞና (simple random sampling) ዘዴ ነው፡፡ ለዚህ ጥናት ስራ ላይ የዋሉት የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች በተጠኝ ተማሪዎች የተፃፉ ድርሰቶች፣ በተማሪዎቹና በአማርኛ ቋንቋ መምህራን ከተሞሉ የፅሁፍ መጠይቆች አስፈላጊ መረጃዎች ተሰብስበው በስህተት ትንተና የአተናተን ዘደ መሰረት በአይነታችው ተለይተው ተተንትነዋል፡፡ ከደርሰቱ እርማት በተገኝው መረጃ መሰረት አጠቃላይ የስህተቶቹ ብዛት 3526 ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የቋንቋ አጠቃቀም ስህተት 1803 (51.13%)፣ የስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም 1034 (29.3313%)፣ የቋንቋ አወቃቀር 577 (16.36%) እና መለየት ያልተቻሉ ስህተቶች 112 (3.18%) ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ተማሪዎቹ ከፃፏቸው ድርሰቶች፣ በተማሪዎችና በመምህርን ከተሞሉ መጠይቆች በተገኙ መረጃዎች መሰረት ዋናዎቹ የስህተት ምንጮች፡- ውስጠ ቋንቋ ተጽዕኖ፣ የአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ የማስረፅ ስልት፣ ስነልቦናዊ እና የአማርኛ ቋንቋ ድምጸልሳናት ተፅዕኖ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በመጨረሻም እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ተማሪዎች ሆሄያትን አንደኛ ደረጃ ላይ እያሉ በትክክትል እንዲለዩ ቢደረግ፣ ለቋንቋ ትምህርት በቂ ክፍለ ጊዜ ቢሰጥ፣ መምህራን ተማሪዎችን በሚያስተምሩበት ጊዜ ስለቋንቋው ጠቀሜታ አስፈላጊውን ግንዛቤ ቢፈጠሩ እና ትምህርቱ በ12ኛ ክፍል የዩኒቭርሲቲ መግቢያ ፈተና እንዲሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሁኔታዎችን ቢያስተካክል የሚሉ የመፍትሄ ሀሳቦች በአጥኚው ተጠቁመዋል፡

Description

Keywords

በአፋርኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ፡አማርኛ ድርሰት

Citation