በ12ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የሰዋሰው ትምህርት ይዘቶች አደረጃጀትና ቀራረብ ግምገማ፤ ግምገማ፤ ከሰነ ትምህርታዊ ሰዋሰው አንጻር
No Thumbnail Available
Date
2003-05
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዓላማ በ1998 ዓ.ም ተሻሽሎ ሥራ ላይ በዋለው የ12ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱ የሰዋሰው ትምህርት ይዘቶችን አደረጃጀት አቀራረብ ከስነ ትምህርታዊ ሰዋሰው አንጻር መገምገም ነው፡፡ ጥናቱ መነሻ ያደረገውም የሰዋሰዋዊ ይዘቶች አደረጃጀትና አቀራረብ ምን ይመስላል ሰዋሰዋዊ ይዘቶቹ ለንቋንቋ ቅርፅ፤ ፍቺና አጠቃቀም ምን ያህል ትኩረት ሰጥተዋል የሚሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ነው፡፡እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ከተተካሪ መጽሐፍፉ በሰነድ ፍተሻ፡ ከመማሪያ መጽሐፉ አሻሻይ ባለሙያና ከናሙና መምህራን በቃለ መጠይቅ እንዲሁም በናሙናነት ከተመረጡ ተማሪዎች በጽሑፍ መጠይቅ አስፈላጊው መረጃ ተሰብስቦና ተደራጂቶ አይነታዊ የምርምር ዘዴን የበመጠቀም በገላጭ የምርምር ስልት የመረጃ ትንተናና የውጤት ማብራሪያ ተሰጥታል፡፡ ሰዋሰዋዊ ይዘቶቹ ክግልጽነት ከትክክለኝነት፤ ከተገቢነት፤ ከተከታታይነት ከዝርዝር ወደ አጠቃላይና ከአጠቃላይ ወደ ገጽታ ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ሰዋሰዋዊ ይዘቶች የታላሚውን ቋንቋ ቅርጽ የሚተነትኑ እንጂ ለመዋቅሩ ፍቺና አጠቃቀም ትኩረት ያላደረጉ ናቸው፡፡ በዚህም የታላሚውን ቋንቋ ትክክለኛ ሰዋሰው ማሳወቅና ይህንን ተጠቅሞ ትግባቦት መፈጸም ከሚሉት የሰዋሰው መማር ማስተማር ዓላማዎች ውስጥ መጀመሪያ ከተጠቀሠው ዓላማ አንጻር ጥሩ ቢሆኑም በሁለተኛው ግን ደካማ ሆነው ተገኝተዋል፡፡በመማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ተካተው የሚገኙት ሰዋሰዋዊ ይዘቶች ከደረጃው መርሃ ትምህርት ጋር ያልተዛመዱ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ይህም የመማሪያ መጽሀፉ የማሻሻል ስራ ከሰዋሰው ትምህርት ማቅረቢያ ንድፈ ሐሳባዊ መርሆች አንጻር ጥሰት የታየበት ሆኖ ተገኝታል፡፡
Description
Keywords
የሰዋሰው ትምህርት ይዘቶች አደረጃጀትና አቀራረብ ግምገማ፤