የስሜታዊ ብልህነት፣ የመጻፍ ችሎታና የመጻፍ ተነሳሽነት ፆታተኮር ተዛምዶ፤ በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

dc.contributor.advisorፕሮፌሰር ጌታሁን አማረ
dc.contributor.authorበለጠ ሕሉፍ
dc.date.accessioned2025-02-14T06:13:12Z
dc.date.available2025-02-14T06:13:12Z
dc.date.issued2024-06
dc.description.abstractየጥናቱ ዋና ዓላማ የስሜታዊ ብልህነት፣ የመጻፍ ችሎታና የመጻፍ ተነሳሽነት ያላቸውን ተዛምዶ ከጾታ አንጻር መፈተሽ ነበር፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም ጥናቱ በተለዋዋጮቹ መካከል ያለውን ዝምድና የማሳየት አላማ ስላለው የተከተለው ዲዛይን (ስልት) ተዛምዷዊ ነበር፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2013 ዓ.ም በደሴ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ደረጃ የሁለተኛው ሳይክል ካላቸው ትምህርትቤቶች መካከል በመምህር አካለወልድ የነበሩ ከ11ኛ G እስከ L ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ (107 ወንዶችና 69 ሴቶች በአጠቃላይ 176) ተማሪዎች በቀላል የዕጣ ንሞና ዘዴ የተወሰዱ ናቸው፡፡ ከተሳታፊዎቹ፤ የስሜታዊ ብልህነት መጠይቅና የመጻፍ ተነሳሽነት መጠይቅ እንዲሞሉ እንዲሁም የመጻፍ ችሎታን ለመፈተሽ የሚያገለግል የመጻፊያ ርእስ በመስጠት እንዲጽፉ በማድረግ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተገኙት መረጃዎችም በገላጭ ስታትስቲክስ (በአማካይ ውጤትና በመደበኛ ልይይት)፣ የርስበርስና የጠራ ዝምድናቸውን ለመለየት በፒርሰን የተዛምዶ መለኪያ እንዲሁም በከፊል የተዛምዶ መፈተሻ ዘዴ ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤቶች እንዳመላከቱትም በስሜታዊ ብልህነት፣ በመጻፍ ችሎታና በመጻፍ ተነሳሽነት መካከል ጾታተኮር ዝምድና ታይቷል፡፡ በሌላ በኩል የስሜታዊ ብልህነት ዘርፎች ከመጻፍ ችሎታ ጋር ተዛምዷቸው ከጾታ አንጻር ልዩነት አላቸው፡፡ እንዲሁም የስሜታዊ ብልህነትና የመጻፍ ችሎታ ከተነሳሽነት አንጻር ልዩነት አሳይተዋል፡፡ በመጻፍ ችሎታና በመጻፍ ተነሳሽነት መካከል ጾታን መሰረት አድርጎ ልዩነት አልታየም፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም ጾታ ጣልቃገብ ሲሆን በተላውጦዎቹ መካከል ልዩነት ያሳያል ወደሚልና የስሜት ብልህነትና የመጻፍ ችሎታ ተዛምዶ የሚኖራቸው የመጻፍ ተነሳሽነት ሲኖር ነው ወደሚል ድምዳሜ ተደርሷል፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም አስተያየቶች ተጠቁመዋል፤ የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል፡፡
dc.identifier.urihttps://etd.aau.edu.et/handle/123456789/4173
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.titleየስሜታዊ ብልህነት፣ የመጻፍ ችሎታና የመጻፍ ተነሳሽነት ፆታተኮር ተዛምዶ፤ በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
በለጠ ሕሉፍ.pdf
Size:
6.71 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: