በጋሞኞ ቋንቋ አፈ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች የአማርኞ ቋንቋ መዋቅር እዉቀትና የአማርኞ ዉህድ አህዶችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ

No Thumbnail Available

Date

1990-05

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ

Abstract

በንባብ ሂደትና ርዴት ላይ አሉታዊ ሆነ አወንታዊ ተጽዕኖ ካላቸዉ ቋንቋዊ ገፅታዎች መካከል አንዱ የመዋቅር እዉቀት ነዉ፡፡የዚህ ጥናት አላማም ይህ እዉቀት በአማርኞ የተፃፉ ዉህድ አህዶችን በማንበብና በመረዳት ረገድ አማርኞ ሁለተኞ ቋንቋቸዉ በሆኑ ጋሞኞ አፈ-ፈት ተማሪዎች ላይ ያለዉን ተጽዕኖ ማጥናት ነዉ፡፡ ለጥናቱ የተመረጡት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኞ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ 82 የጋሞ አፈ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች ናቸዉ፡፡በተጨማሪ ለንፅፅር እንዲያመች ጥናቱ 82 የአማርኞ አፈ-ፈት የሆኑ ተማሪዎችን አሳትፍል፡፡ እነዚህ ተጠኝዎች የዝግ ሙከራን፤ከዝግ ሙከራዉ ምንባብ የወጡ የአንብቦ መረዳት ሙከራን እና የተዛቡ አረፍተ -ነገራትን የማስተካክል ሙከራን እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡የእነዚህን ሙከራ ዉጤት ከተጠኝዎቹ 1990 ዓ.ም የአንደኞ መንፈቀ ዓመት ዉጤት ጋር ለማነፃፀር ተሞክሯል፡፡እንዲሁም የተጠኝዎች የአማርኞ ቋንቋ ዳራዊ እዉቀትን ጠቅለል ባለ መልኩ ለማገኘት የሚያስችል መጠይቅ ተዘጋጅቷል፡፡ በእነዚህ የተለያዩ ሙከራዎች፤ ከአጠቃላይ መረጃ አስገኚ መጠይቅና ከአንደኛ መንፈቀ ዓመት የአማርኞ ፈተና ዉጤት በተገኘዉ ዉጤት መሰርት የጋሞኛ አፈ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች በአማርኞ መዋቅር ያላቸዉ እዉቀት የአማርኞ አፈ-ፈት ከሆኑ ተማሪዎች ጋር ሲነፃፀር ያነሰ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡በተለይ ይህ ልዩነት በ"t" ሙከራ አማካይነት ተሰልቶ በተገኘዉ ዉጤት መስረት እጅግ የጎላ መሆኑ በዝግ ሙከራ ዉጤትና የተለያዩ የአስተራረም ዘዴዎች ዉጤት፡ በአረፍተ ነገር ማስተካከል ሙከራ ዉጤት እና በ1ኛ መንፈቀ ዓመት የአማርኞ ቋንቋ ፈተና ዉጤት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በዚህ የአማርኞ አፈ-ፈት ከሆኑ ተማሪዎች ይልቅ፤የአማርኞ ቋንቋ መዋቅር (XCIUAS) እዉቀት አለመዳበር፤በጋሞኛ አፈ-ፈት ተማሪዎች በአማርኞ ዉህድ አሀዶችን አንብቦ መረዳት ላይ የሚኖረዉ ተፅዕኖ ተጠቁሟል፤፤

Description

Keywords

የአማርኞ ቋንቋ መዋቅር

Citation