በተረቶች ውስጥ የታዩ የሥርዓተ ጾታና የሥልጣን ኢፍትሃዊ መስተጋብሮች
No Thumbnail Available
Date
2009-06
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
Abstract
ይህ ጥናት “በተረቶች ውስጥ የታዩ የሥርዓተ ጾታና የሥልጣን ኢፍትሃዊ
መስተጋብሮች” በሚል የተሰራ ነው፡፡ ጥናቱን ለማካሄድ ግላዊና አካዳሚያዊ ገጠመኞች
የገፋፉ ሲሆን እነዚሁ አነሳሽ ምክንያቶች በተረቶች ውስጥ የታዩ የሥርዓተ ጾታና
የሥልጣን ኢፍትሃዊ መስተጋብሮች እንዴት ተሰናስለው እንደቀረቡ በዝርዝርና
በጥልቀት ማሳየት ለሚለው የጥናቱ ዓቢይ ዓላማ ምክንያት ሆነዋል፡፡
ጥናቱ ዓይነታዊ ምርምር ሲሆን መዋቅራዊ ግልጋሎታዊ፣ ድኅረ መዋቅራዊ እና እንስታዊ
ንድፈ ሃሳቦችን ተከትሏል፡፡ ለጥናቱ ያገለገሉ መረጃዎች ከመስክ ከደቡብ ወሎ ሦስት
ወረዳዎች (ተሁለደሬ፣ ኩታበርና ቦረና) በቃለመጠይቅ፣ በተተኳሪ የቡድን ውይይት፣
በመጠይቅ እንዲሁም ከሰነዶች በጥልቅ ንባብ ተሰብስበዋል፡፡ እነዚህ መረጃዎች በመዋቅራዊ
ግልጋሎታዊ እና በሃቲታዊ ትንተና ስልት ተጠንተዋል፡፡ በዚህ መሰረት ወንዶችና ሴቶች
በተረቶች ውስጥ ምን ዓይነት ገጽታ እንደተሰጣቸው፣ ወንዶች በሴቶች ላይ ያላቸውን
የሃብትም ይሁን የሥልጣን የበላይነት በተረቶች ለማስቀጠል የተቀሙባቸው ሥልቶች እና
የሴቶች ብርታት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተወከሉባቸው ተረቶች በስፋት ተዳስሰዋል፡፡
ሥርዓተ ጾታዊ አድልዎ ሰፊ የባህል መሰረት እንዳለው፣ ይህም በተረቶች ውስጥ ተሰናስሎ
እንደቀጠለ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ እንዲሁም በተረቶች ውስጥ ሥርዓተ ጾታና ሥልጣን እርስ
በርስ መስተጋብር ያላቸው መሆኑ በጥናቱ ተገኝቷል፡፡ አባዊው ዓለም ሥልጣኑን
ለማስቀጠል ይመቹኛል ያላቸውን ለምሳሌ አጥፊ ባላቸው ሴቶች ላይ ቅጣት በመሰንዘር፣
የሴቶችን ገጽታ በማበላሸት፣ የሰናይና የእኩይ ሴቶችን ገጠመኝ ከነውጤቱ በማቅረብ፣
የራሱን ገጽታና አስፈላጊነት ከፍ አድርጎ በማሳየት ወዘተ. በሴቶች ላይ ተጽዕኖ
እንደሚያሳድር፣ ይህም በወንድ የበላይነት የተሰራው አባዊው መዋቅር ከነርዕዮተዓለሙ
በተረቶች ውስጥ ተሰናስሎ መቅረቡ ታውቋል፡፡
ሆኖም ተረቶች የሴትን ከወንድ እኩል አለመሆን ለማሳየት ተብለው ቢተረኩም
ከእንስታውያን ፈለግ አንጻር ሲታዩ ሴቶች ብልሆች፣ መፍትሄ አመንጪዎች፣ ለማወቅ ከፍ
ያለ ጉጉት ያላቸው መሆናቸውን ወዘተ. ጥናቱ አሳይቷል፡፡
ይህ የሥርዓተ ጾታና የሥልጣን ኢፍትሃዊነት በሂደት እንዲስተተካከል ብሎም እንዳይቀጥል
የሴቶችን በጎ ገጽታ የሚያጎሉ ተረቶች እየታተሙ በየትምህርት ቤቶች በስፋት ቢሰራጩ፣
በሥርዓተ ጾታ እኩልነት ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ ለሴቶችም ለወንዶችም እኩል ሥልጠና ቢሰጥ፣
የሥርዓተ ጾታ የእኩልነት ጽንሰ ሃሳብ በራስ ባህል ቢቃኝ፣ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም
ለመገንባት ቢሞከር፣ ወዘተ. የሚሉ ይሁንታዎች ተሰንዝረዋል፡፡
Description
Keywords
የሥርዓተ ጾታና