በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቃላትን በሚማሩበት ጊዜ የትኞቹን ብልሃቶች በተደጋጋሚ አብዝተው እንደሚጠቀሙ መለየት (በአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)
No Thumbnail Available
Date
2022-07
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቃላትን በሚማሩበት ጊዜ የትኞቹን ብልሃቶች በተደጋጋሚ አዘውትረው እንደሚጠቀሙ መመርመር ነው፡፡ ተሳታፊዎች በኦሮሚያ ብሔረሰብ ልዩ ዞን በሩፍሴ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም በመማር ላይ ያሉ የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች በአመች ንሞና ዘዴ ተመርጠዋል፡፡ ጥናቱም ገላጭ የምርምር ስልትን የተከተለ ነው፡፡ በጽሁፍ መጠይቅና በቃለ መጠይቅ አማካኝነት የጥናቱ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ እነዚህ መረጃዎችም በአይነታዊና መጠናዊ የመረጃ መተንተኛ ስልቶች ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቃላትን በሚማሩበት ጊዜ ጥቅል አካካሽ ብልሃቶችን 101(144.3%) ያህልጊዜ በመደጋገም ሲጠቀሙ፣ ሌሎቹን ብልሃቶች በተደጋጋሚ አዘውተረው እንደማይጠቀሙባቸው አመላክቷል፡፡ ለዚህ ተግባር እንደምክናየት የቀረቡት የተማሪዎቹ የትውስታ፣ የአዕምሮታዊ፣ የልዕለ አዕምሮታዊ፣ስሜትነክና ማህበራዊ ብልሃቶችን ሲገለገሉ ሁልጊዜ እንደማይጠቀሙበት ሲያሳየን በአንጻሩ ደግሞ የአካካሽ ብልሃት አጠቃቀማቸው በብቃት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህም በመነሳት ተጠኚ ተማሪዎች በተደጋጋሚ አብዝተው የሚጠቀሙት አካካሽ ብልሃቶችን ሲሆን ሌሎቹን ብልሃቶች ግን አዘውትረው እንደማይጠቀሙባቸው ከሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሷል፡፡ የአማርኛ ቋንቋ መማርያ መጽሐፍት አዘጋጆች የቃላት መማር ብልሃቶችን በተመለከተ ስነ-ዘዴዎችን ቀርጸው እንደ አንድ የቃላት ትምህርት ማቅረቢያ ዘዴ ቢጠቀሙበት፣ የቋንቋ መምህራን ተማሪዎችን በራሳቸው ጥረት እንዲሳተፉ ቃላትን የመማር መንገድ ቢያመቻቹላቸውና ክትትል ቢያደርጉላቸው የሚሉ የመፍትሄ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡
Description
Keywords
በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ