የአማርኛ መምህራን በተማሪዎቻቸው የፅሁፍ መለማመጃ ላይ የሚሰጧቸው የፅሁፋዊ ግብረ መልሶች ትንተና (በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ሊባኖስ ወረዳ በደብረ ጽጌ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)
No Thumbnail Available
Date
2023-09
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በተማሪዎቻቸው የጽሁፍ መለማመጃ ላይ የአምርኛ ቋንቋ መምህራን የሚሰጧቸውን የጽሁፍ ግብረመልሶችን መፈተሽ ነው። የጥናቱን አላማ ከግብ ለማድረስ አይነታዊ እና መጠናዊ የአጠናን ዘዴዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። ተጠኚዎቹም በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ሊባኖስ ወረዳ በደብረ ጽጌ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም. የትምሀርት ዘመን ከ9ኛ እሰከ 11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ በማስተማር ላሉት ሁለት በምህራን እና በ9ኛ (ሀ ና ለ) በመማር ላይ ካሉት በናሙናነት የተመረጡት 45 ተማሪዎች በመረጃ ምንጭነት ተሳታፊ ሆነዋል። ተማሪዎቹ የተመረጡት በዕጣ ናሙና አመራረጥ ዘዴ ሲሆን ለናሙና የተመረጡ መምህራን ደግሞ በጠቅላይ የናሙና አመራረጥ ዘዴ ነው፡፡ለጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያ ያገለገሉ የጽሁፍ መጠይቅ ቃለመጠይቅ እና የክፍል ምልከታ ናቸው የተሰበሰቡ መረጃዎችም በአይነታዊ በመጠናዊ እና በገላጭ የመተንተኛ ስልት ተተንትነዋል፡፡ በተማሪዎች የጽሁፍ መጠይቅ ተሞልተው የተመለሱ ጥያቄዎችን ከግብረ መልስ አይነት፣ ከግብረ መልስ አሰጣጥ ባህሪ፣ ከግብረ መልስ ስልቶች ና ከግብረ መልስ የትኩረት አቅጣጫ እንጻር ተተንትነዋል። በእነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እያንዳንዳቸው መምህራን በተማሪዎቻቸው ድርሰት ላይ የግብረ መልስ አይነቶችን እያቀለቃሉ ቢጠቀሙም በአብላጫው ግን አስተካካይ ግብረ መልስን እንደሚጠቀሙ መረጃው ያሳያል። እነዲሁም በዋናነት ስልቶችን መርጦ የማረም ስህተቶችን መጠቀማቸውን ከምልከታውና ከመጠይቆቹ ለምረጋገጥ ተችሏል፡፡ መምሀራኑ በተማሪዎችቸው ጽሁፍ ላይ ትኩረት አድርገው ግብረ መልስ የሚሰጡት በቅርጽ ላይ መሆኑን እና የተሰጠው ምላሽ አዎንተዊ ገጽታ በአብላጫው የተላበሰ መሆኑን ከትንተናው ውጤት ለምረጋገጥ ተችሏል፡፡ ነገር ግን መምህራን ወደ አንዱ የሚያደላ ግብረ መልስ ከሚሰጡ ሁሉንም የግብረ መልስ ኣይነት እንደ ኣስፈላጊነታቸው እያሰባጠሩ ቢሰጡ ውጤታማ የሆነ ግብረ መልስ ማግኘትና የተማሪዎቹ የመጻፍ ክሂል የሚያሰድግ ይሆናል፡፡
Description
Keywords
የጽሁፍ ግብረመልሶችን መፈተሽ