በሲዲምኛ አፍ ፈት የሆኑ ተማሪዎች በአማርኛ ድርሰት ሲጽፉ የሚፈጽሟቸው ሰዋስዋዊ ስህተቶች ትንተና በአዲሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2023-10

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

ይህ ጥናት ዋና አለማ አድርጎ የተነሳው በሲዲማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አዲሬ ሁተኛ ደረጃ ት/ቤት አፊቸውን በሲዲምኛ ቋንቋ የፈቱ የዘጠነኛ ክፍሌ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ድርሰት ሲጽፉ የሚፈጽሟቸውን ሰዋስዋዊ ስህተቶች መለየት ነው፡፡ ይህን አላማ ከግብ ለማግረስ የሚከተሉት የዓላማ ጥያቄዎች፣ የሚለትን ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት በታላሚ ተማሪዎች በተጻፈ ድርሰቶች እና የጽሁፌ መጠይቆች እንዱሁም ከአማርኛ ቋንቋ መምህራን ጋር በተደረጉ የቃለመጠይቅ ምልልሶች መረጃዎች ተሰብስበው ተተንትነዋል፡፡ በድርሰቶቹ ውስጥ የተስተዋለ አጠቃላይ የስህተቶች ዓይነት እና ብዛት የተቆጠሩት በሁለት ዙር በተጻፉት 240 ድርሰቶች ውስጥ ነው፡፡ ታላሚ ተማሪዎች ሁለቱን ድርሰት ለመጻፌ የተጠቀሙባቸው ቃላት ብዛት በአማካይ 92.8 ሲሆን በአንድ ድርሰት በአማካይ የተገኘው ስህተት 33.32 እና የስህተት ድግግሞሹ ደግሞ 36 ነው፡፡ በጥናቱ የታዩ መሠረታዊ የስህተት ዓይነቶቹ የቋንቋ አጠቃቀም ስህተቶች፣ የቋንቋ አወቃቀር ስህተቶቸ እና ምዴብ የላሊቸው ስህተቶች በዋናነት ተለይተዋል፡፡ ከነኚህ ስህተቶቸ በተጨማሪ በተማሪዎች የተሞለ የጽሁፌ መጠይቆች እና የመምህራን ቃሇመጠይቅ ምሌሌስ በዴጋፌ ሰጪ መረጃነት ተተንትኗሌ፡፡ በተሰበሰበው መረጃ መሠረት ሇሰዋስዋዊ ስህተቱ መንስዔ የሆኑት በመረጃዎቹ ትንታኔ መሠረት የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንደሆነ ፣የሲዲምኛ እና የአማርኛ ቋንቋ አናባቢ እና ተናባቢ ሆሄያት (ዴምጾች) ሌዩነት እና የአፌ መፌቻ ቋንቋቸው ሥርዓተ-ጽህፈት ወይም መዋቅራዊ ህግ ጭምር መሆኑ ተደርሶበታል፤በተጨማሪ የመማር ማስተማሩ ሂደት፣ የማስታሪያ ግብዓቶች፣ማህበራዊ እና ሥነልቦናዊ ሁኔታዎች በቀጥታ የስህተት ምንጭ ወይም መንስዔ ባይሆኑም ለአፈጻጸሙ መንገዴ ከፌተዋሌ፤ እነዚህን ችግሮች (ስህተቶች) ከነመንስዔያቸው ለማስወገድ በአፌመፍቻ ቋንቋቸው እና በአማርኛ ቋንቋ መካከል ያለውን የአናባቢ እና ተናባቢ ድምጾች (ሆሄዎች መካከል) ያለውን ልዩነት ከዝቅተኛ ክፍል ጀምሮ ማለማመድ፣በሲዲሚኛ እና በአማርኛ ቋንቋ መካከል ያለውን የመዋቅር ህጎችን ተማሪዎቹ እንዲለዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

Description

Keywords

አፊቸውን በሲዲምኛ ቋንቋ የፈቱ፡ሰዋስዋዊ ስህተቶች

Citation