ሂደት ወዘውግ ተኮር የማስተማር ዘዴ በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ላይ ያለው ሚና (በአጋሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)
dc.contributor.advisor | ግርማ ገብሬ (ዶ/ር) | |
dc.contributor.author | አካል ግርማ | |
dc.date.accessioned | 2023-12-21T12:24:00Z | |
dc.date.available | 2023-12-21T12:24:00Z | |
dc.date.issued | 2023-09 | |
dc.description.abstract | የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የዘጠነኛ ክፍል በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሂደት ወዘውግ ተኮር የማስተማር ዘዴ በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ላይ ያለው ሚና ፈትሿል፡፡ ይህን አላማ ከግብ ለማድረስ ሙከራ ቢጤ የጥናት ንዴፍ (Quasi experimental research design) በመጠቀም ለምፈተሸ ይቻል ዘንድ ተማሪዎችን በቁጥጥር እና በሙከራ ቡድን በሁለት በመክፈል ጥናቱ ተካሂዷል፤ በመሆኑም ምሁራን ባነሷቸው ሀሳቦች በማጎልበት በዋነኝነት ፈተና በደጋፊነት ደግሞ የፅሁፍ መጠይቅና ምልከታ በመጠቀም መረጃ በመሰብሰብና መረጃውን የቲ-ቴስት የመተንተኛ ዘዴ በመጠቀም በአግባቡ ተደራጅተው ትንተና የተደረገባቸው ናቸው፡፡ የተገኘውም ውጤት እንዳመለከተው በሂደታዊ ዘውግ የተማሩት የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች በልማዳዊው (በመርሃ ትምህርቱ) ከተማሩት የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች በተሻለ የመጻፍ ክሂላቸው እንዳሻሻሉ ፣ በቂ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ፣ የመጻፍ ተሳትፏቸው የተሻሻለ መሆኑን አመልክቷሌ ፡፡ በመሆኑም ሂደታዊ ዘውግ የመፃፍ ማስተማሪያ ዘዴን በመጠቀም የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂልን ማሻሻል፣ በቂ ደረጃ ላይ ማዴረስና ተሳትፎቸውን መጨመር ተማሪዎችን ለደረጃቸው የሚመጥን የመጻፍ ክሂል ችሎታ ላይ ማዴረስ ይቻላል የሚል አስተያየት ላይ ተደርሷሌ ፡፡ በዚህም በወጉ ያረሰ እንደልቡ ጎረሰ እንደሚባለው መምህራን ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን በተገቢ ሁኔታ አዲዱስ አሰራሮችን በመጠቀም በተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ላይ መጠቀም ከቻሉ የሚጠበቀውን ውጤት ማምጣት እንደሚቻል በጥናቱ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ | |
dc.identifier.uri | http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1137 | |
dc.language.iso | am | |
dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ | |
dc.subject | ድርሰት የመፃፍ ችሎታ | |
dc.title | ሂደት ወዘውግ ተኮር የማስተማር ዘዴ በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ላይ ያለው ሚና (በአጋሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት) | |
dc.type | Thesis |