በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጹሁፍ ክፍል ድህረ የማስተማር ልምምድ ውይይት የሱፐርቫይዘሮች ምግብ መረጃ ትንተና
No Thumbnail Available
Date
1988
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና
ሥነ-ጹሁፍ ክፍል ድህረ የማስተማር ልምምድ ውይይት የሱፐርቫይዘሮች
ምግብ መረጃ ትንተና
የማስተማር ልምምድ የመምህራን ስልጠና ዋናውናመሰረታዊ ክፍል ነው፡፡
የዚህ ጥናት ዋናው አላማም በማስተማር ልምምድና በሱፐርቪዝን ሂደት ላይ
በማተኮር ድህረ የማስተማር ልምምድ በሱፐርቫይዘሮችና በተማሪ አስተማሪዎች
መካከል የሚኖረውን የምግብ መረጃ ልውውጥ መመርመርና ማጥናት ነው፡፡
በተለይ የምግብ መረጃ ልውውጥ ላይ ትኩረት በማድረግ አቀራረብን ሂደትና የምግብ መረጃውን
ባህሪይ ለመተነትን ተሞክሮአል ጥናቱ የተመሰረተው በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በኢትዮጵያ
ቋንቋዎችና ሥነ-ጹሁፍ ክፍል ላይ ሲሆን መረጃ ሰጢዎቹም የክፍለትምህርት መምህራን
(ሱፐርቫይዘሮች) ሁለተኛ ዓመት የዲፐ መርህ ግብር ተማሪዎች ናቸው፡፡
ከመምህራኑና ሱፐርቫይዘሮች) ከተማሪ አስተማሪዎች የተሰበሰበው መረጃ ተጠናቅሮ
ከተተነተነ በሓላ ለማሳየት እንደቻለው በክፍለ ትምህርቱ ውስጥ የሚገኙት መምህራን
(ሱፐርቫይዘሮች) ለሱፐርቪዥን ተግባር የሚሰማሩ ይሁን አንጂ
ሱፐርቪዥንና የማስተማር ልምምድን ክትል በተመለከተ ባመዛኙ ስልተና ያላቸው ሆነው
ሆነው አልተገኙም፡፡ ስለዚህም በክፍለ ትምህርቱ ውስጥ የቅድመ ትምህርት ልምምድ
ውይይት የተለመደ ባህል ካለመሆኑም በቀር ሱፐርቫይዘሮች በሱፐርቪዝኑ ሂደት ውስጥ
የሚከተልት ስረራታዊ መመዝገቢያ መሳርና ስልት ሌላችው ናችው፡፡በምግበ መርጃ ልውውጡ
ሂደት ውስጥጉልህ የሆነውን ሚና የተወሰነ ነው ከዚህም በቀር በውይይቱ በሱፐርቫይዘሮቹ
ግላዊ ዳኝነት ጎልቶ የሚደመጥ ሲሆን ከዚህም ከግላዊ ዳኝነት በመነጨ ባመዛኙ በተማሪ
አስተማሪዎቹ ደካማ ጎን ላይ ሱፐርቫይዘሮች ምግብ መረጃ ስያተኩር ጣይታል፡፡ በአጠቃላይ
ምግብ-መረጃ ልውውጡ ሱፐርቫይዘሮች ተጽዕኖ የሚመራ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
በመጨረሻም በጥናቱ ሂደት የተሰሩ መጃዎች ከተተነተኑ በሓላ ያሳዩትን ፍንጭ
መሰረት በማድረግ የማስተማር ልምምዱን ከዚህም ገር በተያያዘ መልኩ ሱፐርቪዥኑንና
የምግበ- መረጃውን አቀራረብ በሚመለከት የሚያስተውሉትነ ጉልህ ችግሮች ጠቅለል
አድርጎ በመስቀመጥ ለወደፍት እንዴት መሻሻል እንደሚገባችው የሚጠቅም የመፍቴ
ሀሳብ ቀርቧል፡፡