(በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና እስልምና እምነት ተከታዮች በሚከበሩ) በልደት እና መውሊድ በዓላት ላይ የሚቀርቡ የአማርኛ መዝሙርና ትንተና ::
| dc.contributor.advisor | መሐመድ አሊ | |
| dc.contributor.author | ሔኖክ ደሴ | |
| dc.date.accessioned | 2026-03-09T10:00:40Z | |
| dc.date.available | 2026-03-09T10:00:40Z | |
| dc.date.issued | 2024-01-30 | |
| dc.description.abstract | ይህ ጥናት በልደት እና በመውሊድ በዓላት ላይ የተካሄደ ሲሆን ከሥነቃል ዘውጎች ውስጥ በሚገኙትን መዝሙርና መንዙማ ላይ መሠረቱን ያደረገ ነው። ጥናቱ ይዞት የተነሳው ዋና ዓለም በልደት እና መውሊድ በዓላት ላይ የሚቀርቡ መዝሙራትና መንዙማዎች ይዘትን ከሚያነሱት ሃይማኖታዊ ጉዳይ በተጨማሪ ከማኅበራዊ ፋይዳቸው እና ከተግባራቸውን አንጻር በመመርመር እና በመተንተን የጋራ እሴቶቻቸውን መለየት የሚል ነው። ለእርሰ ጉዳዩ መመረጥ እንደ አብይ ምክንያት የመዝሙርና መንዙማ የጋራ የሆኑ እሴቶች ማመላከት ላይ የተሰራ ምንም ጥናት ባለመኖሩ ክፍተት እንዳለ መረዳቴ ነው። በቢኤ እና ኤም ኤ ደረጃ በተናጠል የተሰሩ ጥቂት ሙከራዎች ከመደረጋቸው ውጪ ግጥሞች ከሚቀርቡበት ሃይማኖታዊ ገጽታ ባሻገር ምን ዐይነት ተግባራት እና የጋራ እሴቶች አላቸው የሚለውን የሚመልሱ ጥናት አለመሰራቱ ምክንያት ምን ይኾን? የሚለው የምርምር ጥያቄ ደግሞ ሐሳቤን በደንብ አጠናክሮልኛል፡፡ እንደ ፎክሎር ተማሪነቴ ይህንን ጉዳይ ሰፋ አድርጌ ብመለከት ጥናቱ ይህን ክፍተት በመሙላት በኩል ትልቅ አስተዋፆ ይኖረዋል በማለት ይህንን ጥናት ለማድረግ ተነስቻለው። የጥናቱ ዓላም ግብ ይመታ ዘንድ የምርምር ጥያቄዎቹ ምላሽ እንዲያገኙ መረጃዎችን ከቤተ መጽሐፍት፣ከበይነ መረብ እና በቃለ መጠይቅ ተሰብስበዋል። በተጨማሪነት እነዚህ መረጃዎችን ከግብ ለማድረስም በመቅረጸ ድምጽ እና በማስታወሻ ደብተር መረጃዎች ማጠናከር ተችሏል። በእዚህ መልክ የተሰበሰቡ መረጃዎች ሃይማኖታዊ ክብረ በዓል በተባለው የጽንሰ ሃሳብ ማእቀፍ ውስጥ ታይተው መዝሙርና መንዙማን ለመፈከር በሚያስችል በተግባራዊ ንድፈ ሀሰብ በመተንተን በገለጻና በትንተና ሥልት ተብራርተው ቀርበዋል። በአጠቃላይ በጥናቱ ላይ እንደታየው የልደት እና የመውሊድ በዓል የጥበብ ዕሴት መገለጫ፣ የመንፈሳዊ እሴቶች ነጸብራቅ፣ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ገጽታን ማሳያ መሆኑ በጥናቱ ላይ ታይቷል። የመዝሙሮቹ እና መንዙማ ግጥሞች የማኀበረሰ ማትጊያ ፣የማንነት ማጽኛና መገንብያ መሣርያ መሆናቸው የጋራ ከሚደርጋቸው ተግባራትና እሴቶች ተረጋግጧል። | |
| dc.identifier.uri | https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/7931 | |
| dc.language.iso | am | |
| dc.publisher | Addis Ababa University | |
| dc.subject | ይህ ጥናት በልደት እና በመውሊድ በዓላት ላይ የተካሄደ ሲሆን ከሥነቃል ዘውጎች ውስጥ በሚገኙትን መዝሙርና መንዙማ ላይ መሠረቱን ያደረገ ነው። | |
| dc.title | (በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና እስልምና እምነት ተከታዮች በሚከበሩ) በልደት እና መውሊድ በዓላት ላይ የሚቀርቡ የአማርኛ መዝሙርና ትንተና :: | |
| dc.type | Thesis |