የበሳል ድርሰት ምዘና ውጤት አግባብነት፣ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2006-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና አላማ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋና ስነፅሁፍ ትምህርት ክፍል የበሳል ድርሰት ክፍል ፪ ኮርስ ምዘና ውጤቶችን አግባብነት መመርመር ነው፡፡ ይህን አላማ ከግብ ለማድረስ ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ለ1ኛ፣ ለ2ኛና ለ3ኛ አመት የተዘጋጁ 23 የበሳል ድርሰት ምዘናዎችና በእነዚህ ተማሪዎች የተፃፉ 73 በሳል ድርሰቶች በዓላማ ተኮር የናሙና ስልት ተመርጠው ተገምግመዋል፡፡ በተጨማሪም የበሳል ድርሰት ክፍል ፪ ኮርስን ከተማሩ 117 ተማሪዎች በፅሁፍ መጠይቅና በቡድን ተኮር ውይይት፣ እንዲሁም ይህን ኮርስ እነዚህን ተማሪዎች ካስተማሩ 3 መምህራን በቃል መጠይቅ፣ የአፈታተን ሂደቶችን በተመለከተ ደግሞ በክፍል ውስጥ ምልከታ አማካኝነት መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች ከአውድ አግባብነት፣ ከግንዛቤ አግባብነትና ከአስተራረም የአግባብነት ጉዳዮች አንፃር በአይነታዊና መጠናዊ ስልት ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ግኝቶችም የተዘጋጁት ምዘናዎች የተማሪዎችን የበሳል ድርሰት ችሎታ በሚገባ የማይመዝኑ፣ የተግባር መቼቶችንና ግብዓቶችን ለይተው የማያመለክቱ፤ በተማሪዎች የተፃፉ ድርሰቶች ስለ ርዕሰ ጉዳዮች በቂ ሀሳቦችን ያላከተቱ፣ ሀሳቦቹ በወጉ ያልተደራጁና ተገቢ ክለሳ ያልተካሄደባቸው፤ የበሳል ድርሰት ምዘናዎች አስተራረም ደግሞ በግልፅ መስፈርቶች ያልተዘጋጁላቸውና በስኬል ያልተደገፉ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ በአጠቃላይም የምዘናዎቹ የአውድ አግባብነት፣ የተማሪዎቹ የአፃፃፍ ሂደት ተገቢነትና የመምህራኑ አስተራረም ትክክለኛነት ዝቀተኛ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ በሌላ አገላለፅ ለተማሪዎቹ የተሰጡት ውጤቶች የተማሪዎችን የመፃፍ ችሎታ በትክክል የማያመለክቱ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ የጥናት ግኝቶች መሰረት በማድረግም የሚዘጋጁት የበሳል ድርሰት ምዘናዎች በድርሰት መፃፍ ተግባራት ላይ የሚያተኩሩ፣ የተግባራቱ መመሪያዎች የምዘና መቼቶችን በዝርዝር ለተማሪዎች የሚገልፁ፣ ተማሪዎች ደጋግመው እንዲያቅዱና እንዲከልሱ የሚጋብዙ፣ መምህራን የተማሪ ድርሰቶች በግልፅ መስፈርቶችና ስኬሎች የሚያርሙ እንዲሆኑ በመፍትሔነት ቀርበዋል፡፡ በመጨረሻም የተማሪዎችን የበሳል ድርሰት ምዘና ውጤቶችን አግባብነት የበለጠ በመረዳት ተገቢ ማስተካከያ ለማድርግ እንዲቻል የወደፊት የምርመር የትኩረት አቅጣጫዎች ተጠቁመዋል፡፡

Description

Keywords

የበሳል ድርሰት ምዘና

Citation