በጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የማዳመጥ ክሂል ትምህርት የክፍል ውስጥ አተገባበር ፍተሻ (በተመረጡ አራት የመጀመሪያ ትምህርት ቤቶች ተተኳሪነት)
No Thumbnail Available
Date
2023-09
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የማዳመጥ ክሂል ትምህርት የክፍል ውስጥ አተገባበርን መፈተሽሸ ነው፡፡ ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ ገላጭ የምርምር ዘዴን ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ለዚህም ጥናቱ በሚያካትታቸው አራት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በ8ኛ ክፍል የሚያስተምሩ የአማርኛ ቋንቋ መምህራንን የማዳመጥ ክሂል ትምህርት የክፍል ውስጥ አተገባበር ፈትሹአል፡፡ በጥናቱ መስቃን ወረዳንና በውስጡ በሚገኙ የተመረጡ የ8ኛ ክፍልን በአመቺ ናሙና የተመረጡ ሲሆን በጥናቱ የተካተቱትም ትምህርት ቤቶች በቀላል የእጣ ናሙና የተመረጡ ናቸው፡፡ በተመረጡበት ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ከሚያስተምሩ መምህራን በየትምህርት ቤቱ አንድ አንድ በድምሩ አራት ሲሆኑ፣ በጠቅላይ ናሙና ተወስደው በጥናቱ ተካተዋል፡፡ እንዲሁም ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች አንድ አንድ ምድብ በቀላል የአእጣ ናሙና በመውሰድ ከየምድቦቹ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በታች ያህሉ በጥናቱ ለማካተት ሲባል በአላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ዘዴ ከየምድቡ 20 በድምሩ 80 ተማሪዎች በጥናቱ ተካተዋል፡፡ ለጥናቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎችም በተደጋጋሚ በተካሄደ የክፍል ውስጥ ምልከታና በመምህራንና በተማሪዎች የፅሑፍ መጠይቅ መሰረት መረጃውን ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ ከእነዚህም መረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያዎች የተገኙትን ምላሾች በቁጥርና በመቶኛ በማስቀመጥ በገለፃ/ በአይነታዊ /መተንተኛ ዘዴ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ በዚህም መሰረት በመምህራንና በማዳመጥ ክሂል አተገባበር መካከል የሚታዩትን በርካታ ክፍተቶችና ጉድለቶች በራሳቸው በመምህራኑ ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ መምህራን ከላይ የሚታዩባቸውን ችግሮችና ክፍተቶች ለመመልከት ራሳቸውን በተለያዩ ስልጠናዎች በየደረጃ የንባብ ክህሎታቸውን ቢያሻሽሉና በተለያዩ ልምድ ልውውጦችን ቢያደርጉ የማዳመጥ ክሂል ትምህርት አተገባበር የተዋጣለት ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ ይጠቁማል፡፡
Description
Keywords
የአማርኛ ቋንቋ የማዳመጥ ክሂል