አንብቦ መረዳት እና የመጻፍ ክሂል ቅንጅታዊ የይዘት አቀራረብ ትንተና በ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ተተኳሪነት (በ2015 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የታተመ)
dc.contributor.advisor | አቶ ደረጀ ገብሬ | |
dc.contributor.author | ሰይድ አሊ ይመር | |
dc.date.accessioned | 2025-01-14T08:12:28Z | |
dc.date.available | 2025-01-14T08:12:28Z | |
dc.date.issued | 2023-08 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናታዊ ፅሑፍ ዋና ዓላማው በ2015 ዓ/ም ታትሞ በስራ ላይ የዋለው የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ መፅሀፍ ውስጥ የአንብቦ መረዳትና የመፃፍ ክሂሎች ቅንጅታዊ የይዘት አቀራረብ መፈተሽ በ8ኛ ፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሀፍ ተተኳሪ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካትም በሰነድ ፍተሻ እና በቃለመጠይቅ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የጥናቱ ዓላማ በተማሪው መማሪያ መፅሀፍ ውስጥ የመፃፍ ክሂልና የአንብቦ መረዳት ክሂልን አዋህዶ ይዘቶችንና መልመጃዎችን መቅረባቸውና አለመቅረባቸው መመርመር ፤የአንብቦ መረዳት እና የመፃፍ ክሂል አቀናጅቶ ለማስተማር የቀረቡ ምንባቦች የቋንቋ ግልፅነት ማየትና ሁለቱን ክሂሎች አቀናጅቶ ለማስተማር የቀረቡትን መልመጃዎች ግልፅነት መመርመር ነው፡፡ ይህንን ጥናታዊ ፅሁፍ ከፍፃሜ ለማድረስ አጥኝው የተጠቀመ የመረጃ መተንተኛ ዘዴዎች መጠናዊ የምርምር ዘዴ እና ዓይነታዊ የምርምር ዘዴዎች ናቸው፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ሰነድ ፍተሻ እና ቃለ መጠይቅ ናቸው። ከመረጃዎቹ የተገኙት ውጤቶች የሚያመለክቱት አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂልን የሚመለከቱ ይዘቶች አቀራረብ ለመማር ማስተማሩ ሂደትም ሆነ ለተማሪዎቹ ልምምድ አመቺ መሆናቸውን፤ አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂልን የሚመለከቱ ይዘቶችና መልመጃዎች አቀራረብ የተማሪዎችን ደረጃ፣ዕድሜና ችሎታ እንዲሁም ዳራዊ እውቀታቸውን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ መሆናቸውን፤የመማሪያ መጽሀፉ አቀራረብ አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂሎች በተቀናጀ መልኩ እንደተዘጋጁና የማስተማሪያ መሳሪያዎቹ አንብቦ የመረዳትንና የመጻፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ለማስተማር እገዛ እንዳላቸው ጥናቱ ፍተሻ አድርጓል፡፡ በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ መጨረሻ ውጤት የሚያሳየው የአንብቦ መረዳት እና ለፅህፈት ክሂል አቀናጅቶ ለማስተማር የቀረቡት ምንባቦች ቋንቋውን እንደሚረዱት ሆኖ ቀርቧል፡፡ቢሆንም የተወሰኑ ይዘቶች እና መልመጃዎች የቋንቋ ግልፅነት የሌላቸው መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡ በመጨረሻም ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ የሚሰጠው ማሻሻያ ሃሳብ ፤ተማሪዎች አንብበው የተረዱትን ሀሳብ በፅሁፍ ለመግለፅ ይዘቶች እና መልመጃዎች በሰፊው ቢዘጋጅ እና ተቀናጅተው ቢቀርቡ፡፡ የአንብቦ መረዳት እና የፅህፈት ክሂልን በቅንጅት ለማስተማር የቀረቡት ምንባቦች የሃሳብ ግልፅነት የሌላቸው መሆኑን ሲያሳይ ፤ምንባቦች ተሻሽላው ቢቀርቡ በማለት ጥናታዊ ፅሁፍ የመፍትሔ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ | |
dc.identifier.uri | https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/4088 | |
dc.language.iso | am | |
dc.publisher | አዲስ አባባ ዩኒቨርሲት | |
dc.subject | አንብቦ መረዳት | |
dc.title | አንብቦ መረዳት እና የመጻፍ ክሂል ቅንጅታዊ የይዘት አቀራረብ ትንተና በ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ተተኳሪነት (በ2015 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የታተመ) | |
dc.type | Thesis |