የቃላት ትምህርት ይዘቶች አደረጃጀትና አቀራረብ ግምገማ በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በ2015 ዓ.ም ስራ ላይ በዋለው አዲሱ የ6ኛ ክፍል አማርኛ እንደ አፍ መፌቻ ቋንቋ መማሪያ መጽሀፍ ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2022-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና አላማ የቃላት ትምህርት ይዘቶች አደረጃጀትና አቀራረብ ግምገማ በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በ2015 ዓ.ም ስራ ላይ በዋለው አዲሱ የ6ኛ ክፍል አማርኛ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ መማሪያ መጽሀፍ ተተኳሪነት፡፡ ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ ጥናቱ የተከተለው ገላጭ የምርምር ዘዴን ነው፡፡ ጥናቱን ከግብ ለማድረስም የተለያዩ ምሁራን ስለቃላት ትምህርት ይዘት አደረጃጀትና አቀራረብ ባነሷቸው ንዴፈ ሀሳባዊ መስፈርቶችና መርሆዎች ላይ በመመርኮዝ በመማሪያ መጽሀፍ ላይ የሠነድ ፍተሻ በማድረግ እንዲሁም ለመጽሀፍ አዘጋጅና ለመምህራን ቃለመጠይቅ በማድረግ አስፈለጊው መረጃ ተሰብስቧል፡፡ በመቀጠልም ከሰነድ ፍተሻና ከቃለ መጠይቅ የተገኙትን መረጃዎች በአይነት በአይነት በመመደብ የመተንተን ስራው ተከናውኗል፡፡ የትንተናው ውጤትም በመማሪያ መጽሀፉ ውስጥ የቀረቡት የቃላት ትምህርት ይዘቶች አደረጃጀትን በተመለከተ በጥሩ ሁኔታ የተደራጁ መሆናቸው፤ የቃላት ትምህርት አቀራረብን በተመለከተ በፍች ዝምድና ከማቅረብ አንጻር በመማሪያ መጽፉ ውስጥ የቀረቡት የቃላት ትምህርት ተግባራት አቀራረብ ችግር ያለበት መሆኑ፤ በመዝገበ ቃላት አስደግፎ ከማቅረብ አኳያ በመማሪያ መጽሀፈ ውስጥ በመዝገበ ቃል በመደገፍ የቀረቡት የቃላት ትምህርት ይዘቶች በቁጥር አነስተኛ ከመሆናቸውም በላይ በግልጽ መመሪያ አለመቅረባቸው ክፍተት መሆኑ፤ ግልፅ በሆኑ መመሪያዎች ከማቅረብ አኳያ መጽሀፉ የቃላት ትምህርት ይዘት ተግባራትን በግልጽ መመሪያዎችና ምሳሌዎች የማቅረብ ክፍተት ያለበት መሆኑ በድክመት ተነስቷል፡፡

Description

Keywords

የቃላት ትምህርት ይዘቶች አደረጃጀትና አቀራረብ

Citation