የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ግምገማ ለኢ-አፍ ፈት ተማሪዎች በደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ተዘጋጅቶ በ2015 ዓ.ም ስራ ላይ በዋለው 7ኛ እና 8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት ተተኳሪነት
dc.contributor.advisor | ጌታሁን አማረ (ፕ/ር) | |
dc.contributor.author | አበበ ሾይሻ | |
dc.date.accessioned | 2024-09-26T06:02:31Z | |
dc.date.available | 2024-09-26T06:02:31Z | |
dc.date.issued | 2024-08 | |
dc.description.abstract | በዚህ ጥናት ለኢ-አፍ ፈት ተማሪዎች በደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ተዘጋጅቶ በ2015 ዓ.ም ስራ ላይ በዋለው 7ኛ እና 8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍት ውስጥ የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ተገምግሟል፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሳካት የቋንቋ ምሁራን ያቀረቧቸውን ንድፈ ሀሳቦች መሰረት በማድረግ በተተኳሪ መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ የተካተቱ ሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ተገምግሟል፡፡ ጥናቱን ከዳር ለማድረስ ሰነድ ፍተሻ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን የተገኙ መረጃዎች አይነታዊ ምርምር ዘዴን በመጠቀም በገላጭ ስልት ተተንትነዋል፡፡ ከጥናቱ የተገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው የይዘቶቹ አቀራረብ በተመለከተ በታላሚዎቹ መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ ከቅደም ተከተላዊ አካሀድ አንጻር ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ ከቀረበው ይልቅ ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር ዘዴ የቀረበው ይዘት አብዛኛውን ክፍል የሚሸፍን ሲሆን ከትኩረት አንጻር ደግሞ ውጤት ተኮር በሆነ መንገድ ከቀረበው ይልቅ በሂደት ተኮር ዘዴ የቀረበው ሰፍውን ክፍል እንደሚሸፍን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከአደረጃጀት አንጻር ደግሞ አብዛኛዎቹ ሰዋስዋዊ ይዘቶች በተለያዩ ምዕራፎች እየተደጋገሙ መቅረባቸውን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ምንም እንኳን ይዘቶቹ ሚዛናዊና ተመጣጣኝ ባይሆኑም ሁሉንም የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት መንገዶችን አካተው መያዙ፤ ሰዋስው ይዘቶቹ በምሳሌዎች እየታገዙ መቅባቸው፣ ወዘተ እንደ ጠንካራ ጎን የታዩ ይዘቶች ሲሆን የቃላት ትምህርት ከአውድ ውጪ መሰጠት፣ አንዳንድ መመሪያዎችና ይዘቶች ግልጽ አለመሆን፣ የተወሰኑ ይዘቶች መቅረብ የሚገባው መርህ እያለ ያለብስለት መቅረብ፣ ወዘተ እንደ ደካማ ጎን የተነሱ ናቸው፡፡ በተተኳሪ መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ የተካተቱ ሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አብዛኞቹ ተከታታይነት ኖሯቸው የተደራጁ ቢሆኑም ድግግሞሽ አግኝተው የተደራጁ ሰዋስው ትምህርት ይዘቶች በሁሉም ምዕራፎች እና ክፍል ደረጃዎች ተከታትለው አለመደራጀታቸውን፤ “በአረፍተ ነገር” ላይ የሚያተኩሩ ይዘቶች ስፋትና ጥልቀት እንዲሁም የአቀራረብ ለውጥ (ተለጣጣቂነት) ይዘው ተደራጅተዋል፡፡ ባጠቃላይ በተተኳሪ መማሪያ መጽሐፍት ውስጥ የተካተቱ ሰዋስው ትምህርት ይዘቶችን መርሃ ትምህርቱን መሰረት አድርገው ተደራጅተው የቀረቡ ሲሆን በሁሉም አቀራረብና አደረጃጀት ስልቶች መቅረባቸው የሚበረታታ ነው፡፡ በመጨረሻም በይዘቶቹ አቀራረብና አደረጃጀት ዙሪያ የታዩ ደካማ ጎኖችን ለማሻሻል ይረዳሉ ተብለው የታመኑባቸው መፍትሄ ሀሳቦች ተሰንዝረው ጥናቱ ተጠናቋል፡፡ | |
dc.identifier.uri | https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/3476 | |
dc.language.iso | am | |
dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ | |
dc.subject | ሰዋስው ትምህርት ይዘቶች | |
dc.title | የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ግምገማ ለኢ-አፍ ፈት ተማሪዎች በደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ተዘጋጅቶ በ2015 ዓ.ም ስራ ላይ በዋለው 7ኛ እና 8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት ተተኳሪነት | |
dc.type | Thesis |