በ2014 ዓ ም በታተመው የዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ እንደ ፌዴራል ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍና ለዚሁ ክፍል በተዘጋጀው መርሀ ትምህርት መካከል ያለው የመጻሐፍ ክሂል ተጣጥሞሽ

dc.contributor.advisorደረጄ ገብሬ
dc.contributor.authorተረፈ ኤርሰዶ
dc.date.accessioned2023-12-22T09:23:55Z
dc.date.available2023-12-22T09:23:55Z
dc.date.issued2023-10
dc.description.abstractይህ ጥናት በ2014 ዓ ም በትምህርት ሚኒስቴር ታትመው በ2015 ዓ ም ለሙካራ በጥቂት የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የስርጭት ሽፋን ባገኙ የ9ኛ ክፍል አማርኛ እንደ ፌዴራል ቋንቋ መርሀ ትምህርትና የመማሪያ መጽሀፍ መካከል ያለው የመጻፍ ክሂል ተጣጥሞሽ የሚል ነው፡፡የጥናቱ ዓላማ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱም የትምህርት መሳሪያዎች መካከል ያለውን የመጻፍ ክሂል ተጣጥሞሽ መፈተሸ ነው፡፡የጥናቱ ንድፍ መረጃዎቹ ከሰነድና ቃለ መጠይቅ የተገኙ እንደ መሆናቸው መጠን የመጣጣሙን ጥልቀትና አሳሳቢነት ማሳየትን ስለሚሻ ንድፉ ገላጭ የሚባለው ነው፡፡ የጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ሰነድ ፍተሻ እና ቃለ መጠይቅ ናቸው፡፡ ሰነድ ፍተሻ ዋና የመረጃ ምንጭ ሲሆን ቃለመጠይቅ ደግሞ ደጋፊ ነው፡፡ቃለ መጠይቁ የተከናወነው ለሙከራ ትግበራ በተመረጠ ትምህርት ቤት አማርኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራንን በመጠቀም ነው፡፡የመረጃ አተናተን ዘዴው አይነታዊ የሚባለው ነው፡፡ምክንያቱም መረጃዎቹ አሃዝን መሰረት ያልደረጉ በመሆናቸው ነው፡፡ ጥናቱ አዎንታዊም አሉታዊም ውጤት አሳይቷል፡፡በአዎንታ በኩል ከይዘት ተገቢነት አንጻር ለአንቀጽና ለድርሰት ትምህርቶች የጎላ ድርሻ ተሰጥቷቸዋል፡፡”መርሀ ትምህርት” መባል ያለበት በክፍለ የመምህር መምሪያ መጽሀፍ ውስጥ “ስርዓተ ትምህርት” ተብል ተቀምጧል፡፡ “መርሀ ትምህርት”ተብሎ በባል ያለበት ነው፡፡የጽህፈት ትምህርት ርዕሰ ጉዳይ በመርሀ ትምህርቱ በክፍል አራት ተፈጥሯዊውን የቋንቋ ለመዳ ቅደም ተከተል ይዞ የተቀመጠ ቢሆንም በተማሪው መጽሐፍ በክፍል አምስት መቀመጡ ከተፈጥሯዊነትም ሆነ ከትምህርት መሳሪያዎቹ የይዘት ቅደም ተከተላዊ ተጣጣሚነት አንጻር ክፍተት ያሳየ ያለ መጣጣም ነው፡፡ከፍተኛ የአረዳድ ችግር የማስከተል አቅም ባይኖራቸውም መርሀ ትምህርቱ ድርሰት በሚል ርዕስ ሰጥቶ እያለ የተማሪው መጽሀፍ አንቀጽ ያላቸው፣የድርሰት አይነቱ ሳይለይ “ድርሰት ጻፉ” የሚለ ትዕዛዞች፣የጽህፈቱን ደረጃ ሳይለዩ “ጻፉ” ወይም “በጽሁፍ ግለጹ” በሚል የቀረቡ መልመጃዎች በመምህራኑና በያዙት የሀሳብ ስፋት የሚወሰኑ ጽሁፎች ቢሆኑም አይነታቸው አንቀጽ፣ድርሰት…በሚል ተለይቶ አለመገለጽ የሚሉ ይገኙበታል
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1148
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.subjectየመጻፍ ክሂል፡ለድርሰት ትምህርቶች
dc.titleበ2014 ዓ ም በታተመው የዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ እንደ ፌዴራል ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍና ለዚሁ ክፍል በተዘጋጀው መርሀ ትምህርት መካከል ያለው የመጻሐፍ ክሂል ተጣጥሞሽ
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ተረፈ ኤርሰዶ.pdf
Size:
594.14 KB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: