የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብ እና አደረጃጀት ትንተና (በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ2015 ዓ.ም.፣ ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል በተዘጋጁት የአማርኛ መማሪያ መጻሕፍት ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2024-08

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዐቢይ ትኩረት በ2015 ዓ.ም. በአማራ ክልል ስራ ላይ በዋሉት የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ትንተና ነው፡፡ የጥናቱ ዝርዝር ዓላማዎችም በመማሪያ መጻህፍቱ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ይዘቶች የአቀራረብ መርሆዎችን ተከትለው መቅረባቸውን፣ የሰዋሰው ይዘቶቹ የአደረጃጀት መርሆዎችን ተከትለው መቅረባቸውን መተንተን እና በመጻህፍቱ ውስጥ ምን ምን ሰዋስዋዊ ይዘቶች እንደቀረቡ መፈተሽ የሚሉት ናቸው፡፡ የጥናቱ ዋና የመረጃ ምንጮች የመማሪያ መጻኅፍቱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በቃለ-መጠይቅ መረጃውን ለማጠናከር ተሞክሯል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ በአይነታዊ ወይም በገላጭ የምርምር ዘዴ ተተንትኗል፡፡ በዚህም መሰረት በተተኳሪ መጻህፍቱ ውስጥ የቀረቡ የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብ፣ ከግልፅነት፣ ከትክክለኛነት፣ ከተመጣጣኝነትና ከተገቢነት አንጻር ትተንትኗል፡፡ እንዲሁም የሰዋሰው ይዘቶቹን አደረጃጀት፣ከተከታታይነት፣ከተለጣጣቂነት፣ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ፣ ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር አንጻር ያላቸው ገጽታ ምን እንደሚመስል ተፈትሷል፡፡ ይህን ለማሳካትም ጥናቱ በመማሪያ መጻህፍቱ ውስጥ የቀረቡ የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት በክለሳ ድርሳናት ከቀረቡ ጽንሰሀሳቦች አንጻር እየታዩ የተተነተኑ ሲሆን፣ በናሙናነት ከተመረጡ መምህራን በቃለ-መጠይቅ በተገኙ ምላሾች ትንተናውን ለማጠናከር ተሞክሯል፡፡ በመሆኑም የሰዋስዋዊ ይዘቶቹን አቀራረብ በሚመለከት መማሪያ መጻህፍቱ ውስጥ ከግልጽነት፣ ከትክክለኛነት፣ ከተመጣጣኝነትና ከተገቢነት አንጻር ችግሮች እንዳሉ ከትንተናው ውጤት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከአደረጃጀት አንጻርም፣ የተካተቱ ሰዋስዋዊ ይዘቶ ከተከታታይነት፣ ከተለጣጣቂነት አንፃር ችግሮች ያሉ መሆኑ፣ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ እና ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር አደረጃጀቶች ተመጣጣኝ ሆነው ያለመቅረብ /በሰባተኛ ክፍል መማሪያ መጽሀፍ ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር አደረጃጀት ስልት በስፋት ሲገኝ፣ ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ አደረጃጀት ስልት የተዘጋጁ ስድስት ይዘቶች ብቻ ናቸው፡፡ በስምንተኛ ክፍል ደግሞ ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ አደረጃጀት ስልትበስፋት ሲገኝ ከአተቃላይ ወደ ዝርዝር የተደራጁ ሁለት ይዘቶች ብቻ/ ችግሮች እንዳሉ ለማየት ተሞክሯል፡፡ በመጨረሻመም በዚህ ጥናት ውስጥ በሰዋስ ይዘቶች አደረጃጀት ላይ የታዩ ድክመቶችን ለማሻሻል ያስችላሉ ተብሎ የታመነባቸው የመፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡፡ የመጀመሪያው በጥናትና ምርምር ውጤቶች የተጠቆሙ አስተያየቶችን ወስዶ በዝግጅት ወቅት ተግባር ላይ ማዋል፣ ሌላው መማሪያ መጻህፍት ሲዘጋጁ በተቻለ መጠን የአቀራረብና የአደጃጀት መርሆዎችን ተከትለው ቢዘጋጁ የሚሉት ናቸው፡፡

Description

Keywords

Citation