የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች የንባብ ተነሳሽነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ተዛምዶ (በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ቦሌ ቃለ ሕይወት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በሰባተኛ ክፍል ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የማንበብ ተነሳሽነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ መካከል ያለውን ዝምድና መፈተሽ ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም መጠናዊ ምርምርን ብሎም ገለፃዊ የምርምር ስልት ተግባራዊ ሆኗል፡፡ የጥናቱ ተተኳሪዎችም በቦሌ ክፍለ ከተማ በቦሌ ቃለ ሕይወት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም በመማር ላይ የሚገኙ 154 የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ በጠቅላይ ንሞና ተመርጠው የጥናቱ ተሳታፉዎች ተደርገዋል፡፡ ከተጠኚ ተማሪዎች በፅሁፍ መጠይቅ፣ በቃለ መጠይቅና በችልታ መመዘኛ ፈተናዎች መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹም መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በዳግም ልኬት ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ የትንተናው ውጤት እንዳመለከተውም:- የተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ተነሳሽነት እና አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ዝቅተኛ መሆኑ ነው፡፡ በማንበብ ተነሳሽነት ላይ ተፅዕኖ የሚያደርሱ ችግሮችም:- ተማሪው ለማንበብ ያለው ጥረት፣የቋንቋው መምህራን ተማሪውን ለማነሳሳት ያላቸው ጥረት፣ ወላጆች ልጆቻቸውን የመከታተል ጥረት አነስተኛ መሆኑ እና የአካባቢው ማህበረሰብ ለቋንቋው ያው ዝቅተኛ ግምት ናቸው፡፡ጥሩ የንባብ ተነሳሽነት ያላቸው ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸውና በአንጻሩ ዳግሞ ዝቅተኛ ተነሳሽነት ያላቸው ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው በማንበብ ተነሳሽነትና አንብቦ በመረዳት ችሎታ መካከል ጠንካራ ዝምድና እንዳለ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ከጥናቱ ውጤቱ በመነሳት የመፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡፡

Description

Keywords

የማንበብ ተነሳሽነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ

Citation