ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል እና ተነሳሽነት ለማሻሻል ያለው ተጽዕኖ (በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የተካሄደ ሙከራዊ ጥናት)

dc.contributor.advisorኪቲላ, ታመነ((ተባባሪ ፕሮፌሰር)
dc.contributor.authorተሾመ, አማረ
dc.date.accessioned2019-02-08T08:26:10Z
dc.date.accessioned2023-11-09T04:06:49Z
dc.date.available2019-02-08T08:26:10Z
dc.date.available2023-11-09T04:06:49Z
dc.date.issued2010-06
dc.description.abstractይህ ጥናት ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሳው ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል እና ተነሳሽነትን ከማሻሻል አንጻር ያለውን ተጽዕኖ ለመፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱም ከፊል ሙከራዊ ሲሆን፣ የተካሄደውም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኘው የሸዋሮቢት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በትምህርት ቤቱ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች በአመቺ የናሙና ስልት ከተመረጡ በኋላ፣ በዓላማዊ የናሙና አመራረጥ ስልት በአንድ መምህር የሚማሩ ሶስት ምድብ ተማሪዎች ተለይተው በቅድመ ፈተናው ሂደት ተሳትፈዋል፡፡ ከሶስቱ ምድቦች መካከል በቅድመ የመጻፍ ክሂል ፈተና ተቀራራቢ አማካይ ውጤቶች ያስመዘገቡ ሁለት ምድቦች ከተለዩ በኋላ በተራ የዕጣ ናሙና ስልት አንዱ የሙከራ ሌላኛው የቁጥጥር ቡድን ሆኖ በጥናቱ ውስጥ እንዲሳተፍ ተደርጓል፡፡ በመረጃ መስብሰቢያ ዘዴነት ፈተና ፣ የጽሑፍ መጠይቅ እና ምልከታ ሥራ ላይ ውለዋል፡፡ ፈተናው፣ ቅድመ እና ድኅረ ፈተናን ያካተተ ነው፡፡ ቅድመ ፈተናው የተሰጠበት ዓላማ ተማሪዎች ከሙከራ ጥናቱ በፊት ያላቸውን የመጻፍ ክሂል ውጤት ተቀራራቢ መሆን - አለመሆኑን ለመፈተሽ ሲባል ነው፡፡ የድኅረ ፈተናው ዓላማ ደግሞ የሙከራ እና የቁጥጥር ቡድን ሆነው የተመረጡት ተማሪዎች በተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎች የመጻፍ ክሂልን ከተማሩ በኋላ በመካከላቸው ጉልህ ልዩነት መኖር- አለመኖሩን ለመፈተሽ ነው፡፡ በሌላ በኩል የጽሑፍ መጠይቅ የተማሪዎቹን የመጻፍ ተነሳሽነት ለመለካት የቀረበ ነው፡፡ ተተኳሪ የሆኑት ተማሪዎች ከመጻፍ ልምምዱ በፊት (ቅድመ ጽሑፍ መጠይቅ) እና በኋላ (ድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ) እንዲሞሉ ተደርጓል፡፡ በሌላ መልኩ ምልከታው የተካሄደበት ዋነኛ ዓላማ ሁለቱ ቡድኖች በተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎች የመጻፍ ክሂልን እየተማሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ በቅድመ ፈተና እና በቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በባለብዙ ልይይት ትንተና ዘዴ እንዲሁም በድኅረ ፈተና እና በድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በህብር ልይይት ትንተና ዘዴ እንዲሰሉ ተደርጓል፡፡ የተገኙት ውጤቶች እንደሚያመለክቱት በቅድመ ፈተና እና በቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ ተመጣጣኝ አማካይ ውጤቶች የተመዘገበባቸው ቡድኖች፣ በድኅረ ፈተና (ይዘት፣ አደረጃጀት፣ ቃላት፣ የቋንቋ አጠቃቀም እና ሥርዓተ አጻጻፍ) እና በድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ (ግለ ግንዛቤ፣ ግለ ብቃት እና ግለ መር) የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች ከቁጥጥር ቡድኑ ተማሪዎች ጉልህ የሆነ ልዩነት አሳይተዋል (P= <0.05)፡፡ ይህም ውጤት ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል እና ተነሳሽነት ከማሻሻል አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ሊጠቁም ችሏል፡፡ ከመጻፍ ክሂል እና ከተነሳሽነት አንጻር የተገኙት ውጤቶች ላይ በመመስረት ማብራሪያ እንዲሰጥባቸው ከተደረገ በኋላ፣ በጥናቱ የመጨረሻ ምዕራፍ ማጠቃለያ፣ መደምደሚያ፣ የመፍትሄ ሀሳቦች እና የጥናት ጥቆማዎች እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡en_US
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/16324
dc.language.isoamen_US
dc.publisherAddis Ababa Universityen_US
dc.subjectተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል እና ተነሳሽነትን ከማሻሻል አንጻር ያለውን ተጽዕኖ ለመፈተሽ ነውen_US
dc.titleተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል እና ተነሳሽነት ለማሻሻል ያለው ተጽዕኖ (በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የተካሄደ ሙከራዊ ጥናት)en_US
dc.typeThesisen_US

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
አማረ ተሾመ.pdf
Size:
8.32 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Plain Text
Description: