የአንብቦ መረዳት ክሂል ፍተሻ፤ በፓዊ ወረዳ የፓዊ መሰናዶ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ማሳያነት
No Thumbnail Available
Date
2016-12
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አድስ አባባ ዩኒቨርሲት
Abstract
የዙህ ጥናት ዋና ዓሊማ በፓዊ ወረዳ የፓዊ መሰናዶ ትምህርት ቤት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ አንብቦ የመረዳል ክሂል ደረጃን መመርመር ነው፡፡ የጥናቱ ንድፍ ከመጠናዊ ምርምር የሚመደብ ሲሆን ገሊጭ የምርምር ስልትን ተከትሎ ተካሂዶል፡፡ ጥናቱ ፓዊ መሰናዶትምህርት ቤት በአመቺ ንሞና ዘዴ፣ የጠነኛ ክፍል ተማሪዎች በዓላማ ተኮር የንሞና ንሞና ዘዴ እንዲሁም ተጠኚ ሶስት መማሪያ ክፍሎችን በእጣ (በልተሪ) ንሞና ዘዴ በመምረጥ ተማሪዎችን በመረጃ ምንጭነት አካቷል፡፡ አጥኚው የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ አንብቦ መረዳት ችሎታ ለመለካት የአንብቦ መረዳት ፈተና፣ የንባብ ትምህርት አተገባበርን ለመፈተሸ ክፍል ውስጥ ምልከታ እና ቃለ መጠይቅ ተጠቅሟል፡፡ በጥናቱ ውጤት መሰረትም በጥናቱ የተሳተፉ 194 ተማሪዎች በመጀመሪያው ፈተና (የሚጠበቅ ውጤት 18.75፣ የተመዘገበ አማካይ ውጤት 14.19)፣ በሁለተኛዉ ፈተና (የሚጠበቅ ውጤት 18.75፣ የተመዘገበ አማካይ ውጤት 14.71) በአጠቃላይ ፈተና ውጤት ደግሞ (የሚጠበቅ ውጤት 37.50፣ የተመዘገበ አማካይ ውጤት 28.90) ሆኖ ተመዜግቧል፡፡ ይህም የተመዘገበው በአማርኛ አንብቦ የመረዳት አማካይ ውጤት ከሚጠበቀው ውጤት እንደሚያንስ (ዜቅተኛ መሆኑን) ያመለክታል፡፡ በጥናቱ የተሳተፉ 99 ወንድ እና 95 ሴት በድምሩ 194 የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች አማካይ ውጤት በአጠቃሊይ አንብቦ መረዳት ፈተና ወንድ ተማሪዎች 30.0606 እና ሴት ተማሪዎች 27.6947 ሆኖ ተመዜግቧል፡፡ በተመሳሳይ የባዕድ ናሙና ቲ-ቴስት (Independent Sample t-test) ስታትስቲክስ ውጤት ማየት እንደሚቻለዉ ተጠኚ ተማሪዎች ባስመዘገቡት አጠቃላይ በአማርኛ አንብቦ የመረዳት አማካኝ ውጤትና በሚጠበቀው ውጤት መካከል ያለዉ የልዩነት ጉልህነት ደረጃ የወንድ ተማሪዎች t(98) = 2.393 P<0.018 እንዲሁም የሴት ተማሪዎች t(94) = 2.405 P<0.017 ሆኖ ስለተገኘ ከመቁረጫ ነጥብ (0.05) አንሷል፡፡ ይህም በአማርኛ አንብቦ የመረዳት ችሎታ በወንዶችም በሴቶችም ተማሪዎች የተመዘገበው አማካይ ውጤት ከሚጠበቀው ውጤት በታች (ዝቅ ብሎ) ሆኖ መገኘትና ከሴቶች ይልቅ ወንዶች የተሻለ ውጤት ማስመዜገባቸዉ በስታስቲክስ ጉልህ (ተቀባይነት ያለዉ) መሆኑን ያመለክታል፡፡ በምሌከታ በተገኘዉ ዉጤት መሰረት ተጠኚ መምህራን በቅድመ ንባብ እና በንባብ ጊዜ ተግባራት ላይ ጥቂት ድክመቶች (ወጣገባነት) የተስተዋለባቸው ቢሆንም እንደ አጠቃሊይ ሲታይ ጠንካራ (የተሻለ) መሆናቸዉ ተረጋግጧል፡፡ በተቃራኒው በደህረ ንባብ ትምህርት ተግባራት ደረጃ በጣም ደካማ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በመጨረሻም አጥኝው የጥናቱን ግኝት መሰረት በማድረግ የመፍትሄ ሃሳቦችን ጠቁሟል፡፡
Description
Keywords
በአማርኛ አንብቦ የመረዳት ክሂል