የሀዋሪያው ጴጥሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ስዕላዊ የትምህርት መርጃ መሳሪያ አንብቦ መረዳት ክሂል ያለው አስተዋጾ (በአራተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

dc.contributor.advisorደረጀ ገብሬ
dc.contributor.authorክብነሽ ታደሰ
dc.date.accessioned2023-12-25T05:40:02Z
dc.date.available2023-12-25T05:40:02Z
dc.date.issued2022-07
dc.description.abstractጥናቱ የተከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስልክላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ ስድስት የሀዋሪያው ጴጥሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓመተ ምህረትበመማር ላይ ባሉ የ4ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው ። የጥናቱ አላማ ስዕላዊ የትምህርት መርጃ መሳሪያ አንብቦ መረዳት ክሂል ያለው አስተዋፆ በሙከራዊ የምርምር ዘዴ ለመፈተሸ ነው ። ጥናቱ ከመከናወኑ በፊት ካሉት ሶስት ክፍሎች በቀላል እጣ ናሙና አመራረጥ ስልት የሁለት ክፍል 96 ተማሪዎች ተመርጠዋል ። ጥናቱ ሁለት ቡድኖች የያዘ ሲሆን እነሱም የሙከራ ቡድንና የቁጥጥር ቡድን ናቸው ። በሁለቱ ቡድኖች መካከል የችሎታ ተመጣጣኝነት መኖሩ አለመኖሩን ለመለካት ሲባል ምንባቡ ከተለያዩ ፅሁፎች በመውሰድና በመምረጥ ቅድመ ትምህርት ፈተና ተሰጥቷቸዋል። በቅድመ ትምህርት ፈተና በተገኘው የቲ -ቴስትውጤት እንደሚያሳየው የቁጥጥር ቡድኑ አማካይ ውጤት59.47ሲሆን ልይይቱ ደግሞ 0.12500 ነው ። የሙከራው ቡድኑ አማካኝ ውጤት 59.35 ሲሆን ልይይቱ ደግሞ 0.12500ነው ። የሁለቱንም ቡድኖች አማካኝ ውጤትና ልይይት ግምት ውስጥ በማስገባት በቅድመ ትምህርት ፈተና ውጤት በሁለቱ ቡድኖች መካከል የችሎታ ተመጣጣኝነት እንዳለ ለመረዳት ተችሏል ። ቀጥሎም የሙከራ ቡድኑን በስዕላዊ የትምህርት መርጃ መሳሪያ በመታገዝ አንብቦ መረዳትን ሲማሩ ፣ የቁጥጥር ቡድኑ ቀደም ያለትምህርት መርጃ መሳሪያ አንብቦ መረዳትን ተምረዋል። ሁለቱም ቡድኖች ለሰባት ተከታታይ ሳምንታት ለ14 ቀናት ከተማሩ በኋላ ለሁለቱም ቡድኖች ድህረ ትምህርት ፈተና ተዘጋጅቶ እንዲፈተኑ ተደረጓል ።የድህረ ትምህርት ፈተና የቲ -ቴስትውጤት እንደሚያሳየን የሙከራ / የተጠኚ / ቡድኑ አማካኝ ውጤት 82.3958 ሲሆን ልይይት ደግሞ 7.06426 ነው ። የቁጥጥር አማካኝ የቲ -ቴስትውጤት 66.4583 ሲሆን ልይይቱ ደግሞ 12.18642 ነው ።የሁለቱ ቡድኖች አመካይ ውጤት የሚያሳየንስዕላዊ የትምህርት መርጃ መሳሪያ የተማሪዎችን አንብቦ መረዳት ችሎታ እንደሚያሳድግ ወይም እንደሚያጎለብት ነው። መረጃዎቹም መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በደምዳሜያዊ ስታስቲክስ የቲ -ቴስትተተንትኗል ። በዚህ መሰረት ስዕላዊ የትምህርት መርጃ መሳሪያ የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ በዳግም ልኪት ያሳድጋል /ያጎለብታል/ ፤ እንዲሁም የአንብቦ መረዳት ንዑሳን ክሂሎች ለማዳበርና የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል የጥናቱ ውጤት ያረጋግጣል ። በጥናቱ ግኝት መሰረት ለተማሪዎች አንብቦ መረዳት መሻሻል መፍትሄ የሚሆኑ ሀሳቦችተሰንዝbል:: ከመፍትሔ ሀሳቦቹም ለመምህራን፣ የመማሪያ መፅሐፍት አዘጋጆች፣ ለመርሃ ትምህርት አዘጋጆችና ጥናት አድራጊዎች አራቱን የቋንቋ ክሂሎች አቀናጅቶ ከማስተማር አኳያ በስፋት ቢጠናና ስዕላዊ የትምህርት መርጃ መሳሪያ የማስተማሪያ ስልትን በመተግበር አንብቦ የመረዳት ክሂልን ለማዳበር ተማሪዎች ጥሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ፣ እርስ በእርስ መረጃ እንዲለዋወጡ በማድረግ፣ ትምህርቱን በትኩረት እንዲከታተሉና እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው እና ትምህርቱ ሲዘጋጅ በስዕላዊ መርጃ መሳሪያ ቢዘጋጅ ተማሪዎች ውጤታማ እንደሚሆኑ ይህ ጥናት አስገንዝቧል፡፡
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1150
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.subjectስዕላዊ የትምህርት መርጃ፡አንብቦ መረዳት ክሂል
dc.titleየሀዋሪያው ጴጥሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ስዕላዊ የትምህርት መርጃ መሳሪያ አንብቦ መረዳት ክሂል ያለው አስተዋጾ (በአራተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ክብነሽ ታደሰ.pdf
Size:
2.13 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: