ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ት/ቢሮ በተዘጋጀው የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱ የአፍልቆት ክሂሎችን ለማዳበር የቀረቡ መልመጃዎች አቀራረብና አደረጃጀት ትንተና

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዓላማ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ በሚል ርዕስ ለስምንተኛ ክፍል አዲስ በተዘጋጀው የአማርኛ መማሪያ መጽሀፍ ውስጥ የቀረቡትን የአፍልቆት ክህሎችን ለማዳበር የቀረቡ መልመጃዎች አቀራረብና አደረጃጀት በመፈተሽ፣ የታዩ ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ድክመቶችም መጽሀፉ ሲሻሻል ትኩረት አግኝተው የሚሻሻሉበትን ሀሳብ ለመስጠትና አሁን በማስተማር ላይ ሆነው ይህን ጥናት ሊያገኙ የሚችሉ የክፍሉ መምህራን ሲያስተምሩ የታዩ ክፍተቶችን በራሳቸው ሊሞሉ የሚያስችላቸውን የማሻሻያ ሀሳብ ለመስጠት ነው፡፡ የጥናቱ ዓላማ ከግብ ይደርስ ዘንድ የመረጃ ምንጮቹን የሰነድ ፍተሻና ለክፍሉ መምህራን የሚቀርብ የጽሁፍ መጠይቅ አድርጓል፡፡ በሰነድነት የሚፈተሸውም የስምንተኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሀፍ ነው፡፡ ለጽሁፍ መጠይቅ የመረጃ ምንጭ የሆኑ መምህራን በከምባታ ጠምባሮ ዞን፣በዱራሜ ከተማ አስተዳደር ስር ባሉት አራት የመጀመሪያ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ አማርኛ ቋንቋ ከሚያስተምሩት መምህራን መካከል ተመርጠው የቀረቡ ናቸው፡፡ ከሁለቱም የመረጃ ምንጮች የተሰበሰቡ መረጃዎች በአይነታዊና በመጠናዊ ዘዴዎች በመተንተን በማብራሪያዎች ተደግፈው ቀርበዋል፡፡ ትንታኔው የሚያሳየው ለአፍልቆት ክሂሎች ማዳበሪያነት የቀረቡት መልመጃዎች ከይዘት ምርጫ አንጻር ወቅታዊነት፣ ተገቢነትና ተተግባሪነት ያላቸው ይዘቶች እንደሆኑ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ ጥናቱ ከአደረጃጀትም አንጻር ተከታታይነቱ በጥንካሬ የተገመገመ ነው፡፡ የመናገር ክሂል በይዘት የታጨቀ ነው፡፡ ከክፍል ትምህርቱ ይዘት 33.3% የሚሆነውን የተሸፈነው በንግግር ነው፡፡ ስለዚህ ዝግጅቱ የአደረጃጀት ችግር እንዳለበት ለንግግር ክሂል የተሰጠው ሰፊ ሽፋን ማሳያ ነው፡፡ በተቻለ ፍጥነት መሻሻል ካለባቸው ችግሮች ዋነኛው የንግግርን ሽፋን ማስተካከል ነው፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ የመጽሀፉ ዝግጅት የተለጣጣቂነት ችግር እንዳለበት ያሳያል፡፡ ይዘቱ ከቀላል ወደ ውስብስብና ከባድ ስፋትና ጥልቀት እየጨመረ መሄድ ሲገባው ከአደረጃጀትም ሆነ ከአቀራረብ አንጻር ወጥነት የጎደለው አካሄድ ተከትሏል፡፡ ይህም ክፍተት በሚመለከተው አካል ሊስተካከል ይገባል የሚል አመለካከት ያላቸው የመፍተሄ ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡

Description

Keywords

ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፡የአፍልቆት ክሂሎችን ማዳበር

Citation