በአዲሱ የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃሕፍት ውስጥ የቀረቡት የጽሕፈት ክሂል ትምህርት ይዘቶች አደረጃጃት ንጽጽራዊ ግምገማ

No Thumbnail Available

Date

2016-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

Addis Ababa University

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና በአዲሱ የ9ኛእና የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃሕፍት ውስጥ የቀረቡት የጽሕፈት ክሂል ትምህርት ይዘቶች አደረጃጃት በንጽጽር መገምገም ነው፡፡ ጥናቱ ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህንን አላማ ለማሳካት የተመረጠው ገላጭ የምርምር ንድፍ ሲሆን የተገኙት መረጃዎች ተሰብስበው በመጠናዊና በአይነታዊ የምርምር ዘዴዎች ተተንትነዋል፡፡ ለዚህ ጥናት የተመረጡት የዘጠነኛ እና የአስረኛ (9ኛ-10ኛ) የክፍል ደረጃ መማሪያ መጻሕፍት በ2015ዓ.ም ለሙከራ ስራ ላይ የዋለትን መማሪያ መጻሕፍት በአላማ ተኮር የንሞና ዘዴ ተመርጠዋል፡፡ በእነዚህ ሁለት የክፍል ደረጃዎች ውስጥ መማሪያ መጻሕፍትን በማዘጋጀት ላይ ከሚገኙት ውስጥ አንድ የመማሪያ መጻሕፍት አዘጋጅ ቃለ መጠይቅ ተደረጓል፡፡ ጥናቱ ለማካሄድ በሁለቱም መማሪያ መጻሕፍት የተለያዩ ምዕራፍችና ገፆች ውስጥ የሚገኙትን የመፃፍ ክሂል ትምህርት ይዘቶች በሰነድ ፍተሻ ተለይተው ተሰብስበዋል፡፡ ለጥናቱ የሚያስፈልጉት መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኃላ በይዘት አደረጃጀት መርሆች ትንትናና የአተናተን ዘዴ መሰረት በመማሪያ መጻሕፍት ውስጥ ያሉትና የሌሉት ይዘቶቹ በአይነት ተለይተው ተተንትነዋል፡፡ በተገኘው ውጤት መሰረት በሁለቱም መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ የተካተቱት የጽሕፈት ክሂል ትምህርት ይዘቶች ብዛት 21 ሲሆን አማካኝ የድግግሞሽ መጠናቸውም 87.5% ሆኖ ተከታታይነታቸውን ጠብቀውና ስፋት ጥልቀታቸውን እየጨመሩ የመሄድ ሁኔታ ታይቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን በሁለቱም መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ 29.8% የሚደርሱ የመፃፍ ክሂል ትምህርት ይዘቶች አንዴ ብቻ ቀርበው ሳይደጋገሙ መኖራቸው ለማየት ተችሏል፡፡ ከተደራጁት 21 የየጽሕፈት ክሂል ትምህርት ይዘቶች ውስጥ 9ኙ ብቻ ተለጣጣቂነት ሲቀርቡ የተቀሩት 12ዎቹ ደግሞ ተለጣጣቂነታቸው ሳይጠብቁ የቀረቡ መሆናቸውን ጥናቱ አመላክቷል፡፡ በጥናቱ ውጤት መሰረትም በመማሪያ መጻሕፍት ውስጥ የሚቀርቡ የመፃፍ ክሂል ትምህርት ይዘቶች በሁለም የእርከኑ መጻሕፍት ውስጥ ተለጣጣቂነት/ ቀጣይነት/ እንዲኖራቸው ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እና እንደ አስፈሊጊቱ የተማሪዎች ዳራ መሰረት በማድረግ የጽሕፈት ክሂል ትምህርት ይዘቶች ከዝርዝር ወደ አጠቃላይና ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር ስልት አደረጃጀት አመጣጥኖ ማቅረብ ወደ አንድ ስልት ብቻ አለማመዘን የሚሉት በመፍትሔነት ተጠቁሟል፡፡

Description

Keywords

የ9ኛእና የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ

Citation