የአማርኛ ቋንቋ ሰዋስው የመማር ብልሀቶች ፍተሻ በዎላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ በቅሎ ሰኞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

dc.contributor.advisorፕ/ር ጌታሁን አማረ
dc.contributor.authorኢያሱ ኦንዶሼ
dc.date.accessioned2023-12-07T11:16:53Z
dc.date.available2023-12-07T11:16:53Z
dc.date.issued2023-09-03
dc.description.abstractየዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ በቅሎ ሰኞ ሁለተኞ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ ሰዋስው የመማር ብልሀቶችን መመርመር ነው፡፡ ለዚህም ዘጠነኛ ክፍል ካሉት ከ440 ተማሪዎች መካከል በማሰባጠር 40 ተማሪዎች በዓላማ ናሙና ዘዴ ተመርጣዋል ፡፡ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የፅሁፍ መጠይቅ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የተሰበሰቡ መረጃዎችንም በሁለት ዋና ዋና ብልሀቶች በመክፈል ቀጥተኛ የመማር ብልሀቶች (የማስታወስ፤ አእምሮታዊና የማካካሻ) እና ኢቀጥተኛ የመማር ብልሀቶች (ልዕለ አእምሮታዊ፣ ስሜታዊና ማህበራዊ) መሰረት ዝርዝር ብልሀቶችን በምን ያህል መጠን እንደሚገለገሉባቸው በሰንጠረዥ ተደራጅተው በቁጥርና በመቶኛ ተጠቃልለው እንዲታዩ በማድረግ በገላጭ ዘዴ ተተንትነዋል፡፡ በፅሁፍ መጠይቅ በተሰበሰቡ መረጃዎች ትንተና ውጤት መሰረት የተማሪዎች ቀጥተኛ የመማር ብልሀቶች አጠቃቀም ዝቅተኛ ሲሆን ኢቀጥተኛ ብልሀቶች አጠቃቀም የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ተማሪዎች ከቀጥተኛ መማር ብልሀቶች ውስጥ የሰዋስው ትምህርት ከዚህ በፊት ከሚያውቀት ነገር ጋር ማያያዝን፣ በአእምሯቸው ውስጥ ምስል በመፍጠር ማስታወስን፣ የተለያዩ አካላዊ እንቅስቃሴዎች መጠቀምን፣ ህጎችን ደጋግሞ መፃፍና መናገርን፣ ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር መማርን፣ ጠቃሚ ሀሳቦችን አጠር አድርጎ ማስታውሻ መያዝን፣ ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ጋር ማነፃፀርን፣ ወደ አፍ መፍቻ ቋንቋ መተርጎምንና በፅሁፍ ውስጥ ጠቃሚ የሆኑ ሰዋስዋዊ መረጃዎችን የተለያዩ ምልክቶችን በማድረግ የመጠቀም ብልሀቶችን፤ ከኢቀጥተኛ መማር ብልሀቶች ውስጥ ደግሞ ዓላማ ማዘጋጀትን፣ ትኩረት መስጠትን፣ ማቀድን፣ጭንቀት መቀነስን፣ ራስን ማበረታታትን፣ አዎንታዊ ገለፃ መስጠትን፣ ሀላፊነት መውሰድን፣ ከክፍል ተማሪዎች ጋር መተባበርን፣ መምህሩን መጠየቅንና ማህበራዊ ግንዛቤ ማዳበርን አዘውትረው እንደሚጠቀሙ ለመረዳት ተችሏል፡፡ አብዘኞቹ ተማሪዎች ሌሎችን ዝርዝር ብልሀቶችን አልፎ አልፎ እንደሚገለገሉባቸው የተገኘው ትንተና ውጤት ያመለክታል፡፡ ይህም ብዙ ተማሪዎች ለበርካታ ቀጥተኛም ሆነ ኢቀጥተኛ ብልሀቶች ዕውቀትና ልምድ የሌላቸው መሆኑን ያሳያል፡፡ በመሆኑም መምህራን የተማሪዎቹን የመማር ብልሀት ምርጫ ተረድተው መረጃ በመስጠት ተማሪዎች የተለያዩ ሰዋስው የመማር ብልሀቶች ዕውቀትና ልምድ እንዲያዳብሩ ግንዛቤ ቢያስጨብጡ፤ ተማሪዎች ቀጥተኛ ሰዋስው የመማር ብልሀቶችን በተለይ የማስታወስና የማካካሻ ብልሀቶችን የመጠቀም ፍላጎታቸው አነስተኛ ስለሆነ የቋንቋ መምህራን ተማሪዎች እነዚህን ብልሀቶች በክፍል ውስጥም ሆነ ከክፍል ውጭ እንዲጠቀሙ ሁኔታዎችን ቢያመቻቹ፤ አንዳንድ ተማሪዎች ለመምህሩ ጥያቄ ማቅረብን፣እንቅስቃሴ መጠቀምን፣ ማድመቅ ማክበብን ብልሀቶችን ፈፅሞ ስለማይጠቀሙ መምህራን ተማሪዎቻቸው እነዚህን ብልሀቶች አልፎ አልፎ ቢሆንም እንዲጠቀሙ ቢያበረታቱ፤ እንዲሁም ተማሪዎች አዘውትረው የሚጠቀሙባቸውን ብልሀቶች ተከትለው የሚመጡ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ቢጠብቁ የሚሉ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ ጥናቱ ተጠናቅቋል፡፡
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/348
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.titleየአማርኛ ቋንቋ ሰዋስው የመማር ብልሀቶች ፍተሻ በዎላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ በቅሎ ሰኞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ኢያሱ ኦንዶሼ.pdf
Size:
761.67 KB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: