በክስታኔ ጉራጌ ቋንቋ አፈ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ጽሐፍ ሲጽፉ የሚፈጽሟቸው ስህተቶች ትንተና (በ9ኛ ክፌል ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት አብይ አላማ በጢያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ የክስታኔ ጉራጌ ቋንቋ አፌ-ፈት የሆኑ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ጽሐፍ በሚፅፈበት ጊዜ የሚፈፅሟቸውን ዋና ዋና የስህተት አይነቶች እና የስህተት ምንጮች መለየት ነው፡፡ ይህንም አላማ ከግብ ለማድረስ አጥኚዋ የተጠቀመችው ቅይጥ የምርምር ዘዴን ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በጢያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን የተመረጠውም በአመቺ የናሙና ዘዴ ነው፡፡ በትምህርት ቤቱ ከሚገኙ የክስታኔ ጉራጌ ቋንቋ አፈት ከሆኑ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 60 ተማሪዎችን በእኩል እድል ሰጪ የናሙና ዘዴ በመምረጥና ሶስት የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራንን በጠቅላይ የንሞና ዘዴ በመምረጥ አስፈላጊው መረጃ ተሰብስቧል፡፡ መረጃው የተሰበሰበውም ተጠኚ ተማሪዎችን በሁለት ዙር ጽሐፍ በማጻፍና የጽሐፍ መጠይቅ በማስሞላት እንዲሁም መምህራንን ቃሇለ መጠይቅ በማስሞላት ሲሆን ገላጭ የትንተና ዘዴን በመከተል ትንተናው ተሰርቷል፡፡ ተማሪዎቹ የፃፋቸውን ጽሁፍች በሶስት መምህራን በማሳረም የፈፀሟቸውን ዋና ዋና የስህተት አይነቶችን መለየት ተችላል፡፡ በመረጃ ትንተና ውጤቱ መሰረትም ዋና ዋና የስህተት በአይነቶቹ የሆሄያት አጠቃቀም ስህተት፣ የቃላት ዴግግሞሽ ብዛት፣ የስርዓተ-ነጥብ አጠቃቀም ስህተት፣ የቃላት ድረታ ብዛት፣ የሰዋስው ስህተት እንዲሁም የሀሳብ አገላለፅ ችግር መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ በመረጃ ትንተና ውጤቱ መሰረትም የስህተት ድግግሞሹን ስንመለከት የቃላት ድግግሞሽ 4.87፣ የቃላት ድረታ 3.84፣ የሰዋስው ስህተት 1.97፣ የስርተ-ነጥብ አጠቃቀም ስህተት 4.27፣ የሆሄያት አጠቃቀም ስህተት 9.07፣ እንዲሁም የሀሳብ አገላለፅ ስህተት 1.73 መሆኑን የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡ የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግም መምህራን፣ ተማሪዎቻቸው ፉደላትን በስርዓት እንዱለዩና ፅህፈትን ደጋግመው እንዲለማመዱ ቢያደርጉ፤ መርሐ ትምህርት፣ አዘጋጆች መርሐ ትምህርቱን እንደገና ቢገመግሙት፤ መጽሀፍ አዘጋጆች፣ በመፅሀፍ ውስጥ የተካተቱትን የፅህፈት ትምህርት ይዘቶችን እንደገና ቢገመግሟቸው፤ መልካም ነው የሚል አስተያየቶች ተጠቁመዋል፡፡

Description

Keywords

የጉራጌ ቋንቋ

Citation