የቡርጂ ባህላዊ አስተዳደር እና እምነት
No Thumbnail Available
Date
2003-11
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ
Abstract
ይህ ጥናት የቡርጂ ባህላዊ አስተዳደርና ከአስተዳደር ሥርዐቱ ጋር ተያይዘዉ የሚፈፀሙ እምነታዊ ድርጊቶችን በገለፃ ለማሳየት ይሞክራል፡፡ በመሆኑም ጥናቱ ኳልቴቲቭ (በፍቃደ አባባል ኳልታዊ) የአጠናን ዘዴን(Qualitative Research Methodology) ይከተላል፡፡ የቃል መጠይቅ (Interview) እና የቡድን ዉይይት (Group Discussion) ዋንኞቹ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች(data collection methods )በመሆን አገልግለዋል፡፡ በባህላዊ የ አስተዳደርና የእምነት ሥርዓቶች ዉስጥ የተሳተፉ ፤ በመሳተፍ ላይ ያሉና ባህላዊ ሥርዐቱን ጠንቅቀዉ የሚያዉቁ አምስት ሰዎች የጥናቱ ቁልፍ መረጃ አቀባዮች (Key Informants) ሆነዉ ተመርጠዋል፡፡
በጥናቱም ቡርጂዎች ያልተማከለ የአስተዳደር ሥርዓትን የሚከተሉና የጎሳ፤㝕ኅግና ክልላዊ የሚባሉ ሦሥት ባህላዊ የፖለቲካ ተቋማት ያላቸዉ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በቡርጂ የፖለቲካ ሥርዓት ዉስጥ ጠንካራዉና ወሳኙ የጎሳ አስተዳደር ተቋም መሆኑ በጥናቱ ተገልጧል፡፡ የቡርጂ ባህላዊ አስተዳደር መሪዎች ተቀዳሚ ተግባር ስለ ህዝቡና አከባቢዉ መጻዒ ሁኔታ በማስጠንቆልና በማስተንበይ ህዝቡን፤ የህዝቡን ንብረትን ህዝቡ የሚኖርበተን አከባቢ ፤ወደፊት ይደርሳሉ ከሚባሉ ክፉ አገጣሚዎች (ማለትም ከበሽታ፤ ከጦርነት፤ ከረሀብ ወዘተ ) መካከል መሆኑ ፤ መሪዎቹ ፤በራሳቸዉ ልዕለ ተፈጥሮዊ ሀይል (Super Natural Power)የሌላቸዉ ነገር ግን ተግባራቸዉን የሚያከናዉኑት በጠንቋዮች(Magico Religion) በተንባዮች(Prophtes) እና ጋን (Gann) የሚል ተፈጥሮኣዊ ኃይል አላቸዉ ተብለዉ በሚታመኑ በባህላዉ የእምነት መሪዎች በመታገዝ መሆኑ በጥናቱ የተገለጸ ሌላዉ ነጥብ ነዉ፡፡ የእምነት መሪዎችም ጋን የሚባል ልዕለ ተፈጥሮዊ ሀይል ያላቸዉ መሆኑ ፤ በዚህ ሀይል በመታገዝም ፤በሂዝ ችግሮች ላይ ፈጥነዉ መድረስ፤ ደርሰዉ ከችግሮቹ ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ፤ህዝቡንም ከችግሮቹ መታደግ ፤መመረቅ ፤መባረክ፤መፀለይ የዘዉትር ስራቸዉ እንደሆነ ፤ ይህንን ለመፈፀም ሲሉ ወይም ያሉት እንዲሆንላቸዉ ፤ የለመኑት እንዲሰምርላቸዉ ሲሉ ግን የሚፈፅሙት የተለየ ነገር የለም፡፡ የቡርጂ ባህላዊ አስተዳደር እና የእምነት ተቋማት አንዱ በሌላዉ ዉስጥ ያሉ፤ የሚደጋገፉ ፤እንዲሁም የቡርጂ ህዝቦች በሙታን ሰዎች የሚያምኑ (ancestral worships) መሆናቸዉ በጥናቱ የተገለፀ ሌላዉ ነጥብ ነዉ፡፡ ሙታን ወገኖች ለቡርጂዎች ለፈጣሪ የቀረቡ ፤ ፈጣሪን የሚያማልዱ ፤በህያዊያን ወገኖቻቸዉ ላይ ያሻቸዉን ማድረግ የሚያስችላቸዉ ልዩ ሀይል ያላቸዉ ናቸዉ፡፡ ለወገኖቻቸዉ ሞትና ህይወት፤ ለአካባቢዉ ልማትና ዉድቀት ወዘተ ምክንያቶች የሙታን ወገኖች እርግማንና ምርቃት እንደሆነ ተደርጎ እንደሚታመን ጥናቱ ያሳያል፡፡በቡርጂ ሀገረሰባዊ ኃይማኖት ዉስጥ አንዱ የበላይ ሌላዉ የበታች፤ አንዱ አዛዥ ሌላዉ አዛዥ የሆነበት የአሰራር ስርዓት የለም፡፡
የቡርጂ ባህላዊ የፖለቲካ የእምነት ተቋማት መሪዎቹን የሚቆጣጠሩባቸዉ ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓቶች ያሏቸዉ መሆኑ ፤ እንዲሁም በአሁኑ ዘመን ላይ በተለያዩ የዓለም ሀገሮች ዉስጥ እየተተገበረ ያለዉ የዲሞክራሲ ስርዓት በቡርጂ ባህላዊ አስተዳደርና ስርዓት ዉስጥ ሙሉ ለሙሉ የለም ማለት ባይቻልም፤ለዲሞክራሳዊ የአሰራር ስርዓት መሰረት ሊሆኑ የሚችሉ አንዳንድ እዉነቶች ግን መኖራቸዉን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ የቡርጂ ባህላዊ የፖለቲካና የእምነት ስርዓቶች ሙሉ ለሙሉ የወንድ የበላይነት የሚንፀባረቅባቸዉ መሆኑ በጥናቱ የተስተዋለ ሌላዉ ነጥብ ነዉ፡፡ በመጨረሻም እነዚህ ባህላዊ የፖለቲካና የእምነት ስርዓቶች በአሁኑ ጊዜ በአብዛኞዎቹ (በተለይም በወጣቱ ዘንድ)በዉል የማይታዎቁ፤በሚቀዉቁቱም ዘንድ እየተረሱ ፤መልካቸዉ፤ጠረናቸዉ እየተለወጠ ያለ ስለሆነ ከወዲሁ የሚያዉቁት እንዲያዉቁ፤ በአግባቡ ተቀርፀዉ ቢቀመጡ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለዉም በጥናቱ የተሰነዘረዉ አስተያየት ነዉ፡፡
Description
Keywords
ባህላዊ አስተዳደር እና እምነት