የአማርኛ ሰዋስው ትምህርት የክፍል ውስጥ አተገባበር ፍተሻ (በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረሊባኖስ ወረዳ በድሬ ጅቦ እና በአባገዳ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት የቀረበ ጥናት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የጥናቱ አብይ ዓላማ የመምህራንን የሰዋስው ትምህርት የክፍል ውስጥ አተገባበር በመፈተሽ የተስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ በመጠቆም የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተጠቁመዋል፡፡ ጥናቱ አይነታዊ የምርምር ዘዴን ተግባራዊ አድርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎች ሁለተኛ ቋንቋቸው የሆኑ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እና የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ሲሆኑ እነዚህ ዋነኛ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ጥናቱ ጥያቄ አድርጎ በተነሳባቸው ነጥቦች ዙሪያ የቋንቋ ምሁራን ያቀረቧቸውን ንድፈሃሳባዊ ብያኔዎች መሰረት በማድረግ የሰዋስው ትምህርት አተገባበር በሚለው ርዕስ ስር መነሳት ያለባቸውን ነጥቦች በዝርዝር ለማየት ሞክሯል፡፡ የጥናቱ አብይ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ የክፍል ውስጥ ምልከታ ሲሆን ከተማሪዎች የጽሑፍመጠይቅ እና ከመምህራን በቃለመጠይቅ የተገኙ መረጃዎችም በመጠናዊና በአይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ስልቶች አንድ በአንድ ለመተንተን ተሞክሯል፡፡ ከመረጃ ምንጮቹ የተገኙት መረጃዎችም እርስ በእርስ ባላቸው ተዛምዶ አንድ ላይ በማደራጀት በምዕራፍ አራት ስር ለመተንተን ተችሏል፡፡ ከጥናቱ የተገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው ታላሚዎቹ መምህራን በክፍል ውስጥ በትግበራ ወቅት የሰዋስው ትምህርት ይዘትን ሲያቀርቡ የተለያዩ የማስተማሪያ ስልቶችን አለመጠቀማቸው፣ ተማሪዎች በቡድን እንዲወያዩ እና ሀሳባቸውን በነጻነት እንዲያንጸባርቁ እድል አለመስጠት፣ የሰዋስው ትምህርት አቀራረብ ደረጃዎችን አለመጠቀም፣ እንዲሁም ምጋቤ ምላሽ አሰጣጥ ላይ ድክመት እንዳላቸው መመልከት ተችሏል፡፡በሌላ በኩል ታላሚዎቹ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር ጥሩ መስተጋብር እንዳላቸው ታይቷል፡፡በአጠቃላይ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች በማበረታታት፣ ደካማ ጎኖቹ ደግሞ ሊቀረፉ የሚችሉበትን እና የመማር ማስተማሩን ሂደት የተሻለና ውጤታማ ያደርጋሉ ተብለው ከታመነባቸው ሀሳቦች ውስጥ የመምህራንን የትምህርት ዝግጅት በተመለከተ መምህራኑ ትምህርቱን ከማቅረባቸው በፊት በቂ ዝግጅት ቢያደርጉ፣ የሰዋስው ትምህርቱን ሲያቀርቡ የማለማመጃ ስልቶችን እንደ ምልልስ፣ሚና ጨዋታ፣የመሳሰሉትን እና የአቀራረብ ደረጃዎችን በክፍል ውስጥ በመጠቀም ቢያስተምሩ፣ሰዋስውን በተናጠል ከማስተማር ይልቅ ከቋንቋ ክሂሎች ጋር አቀናጅተው ቢያቀርቡ፣ ወዘተ. የሚሉትን የመፍትሄ ሀሳቦች በመጠቆም ጥናቱ ተጠናቋል፡፡

Description

Keywords

የሰዋስው ትምህርት አተገበባበር

Citation