የአያያዥ ቃላትና ሐረጋት አጠቃቀም ጥናት በአራት የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች በሚገኙ የ11ኛክፍል ተማሪዎች መነሻነት

No Thumbnail Available

Date

2000-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስት

Abstract

ይህ ጥናት የአያያዥ ቃሳትና ሐረጋትና አጠቃቀም በተመለከተ በአዲስ አበባ ከተማ መሰተዳድር ሰር ባሉ የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች በድርሰቶቻቸው ውሰጥ የተገለገሉባቸውን አያያዥ ቃላትና ሐረጋት ከአጠቃቀም ተገቢነት እኳያ ለመፈተሸ የተደረገ ጥናት ነው፡፡ ከተጠኝዎች ተገቢውን መረጃ ለማግኝት ድርሰቶችን ፅፈዋል፡፡ የፅሑፍ መጠይቆችን ምልተዋል፡ ከአማርኛ ቋንቋ መምህሮቻቸውም የቃለ መጠይቅ መልሶች ተገኝተዋል፡፡ ተጠኝዎች በፃፍቸው ድርሰቶች ውስጥ በድምሩ (በአጠቃላይ) 2901 አያያዥ ቃላትና ሀረጋትን ሲጠቀሙ 415ቱ የአጠቃቀም ስህተት/ጉድለት/ ታይቶባቸዋል፡፡ 2486 ያህሉ ደግም በአጠቃቀም ተገቢነት የተመዘገቡ ሲሆን ይህንንም ተገቢ አጠቃቀም በእያያዥ ቃላትና ሀረጋት አመዳደብና አከፍፈል ሂደት ተከፍፍሎ ሲታይ፡- በምድብ ሀ የፅሁፍ ሁነት (event) ሲዘገብ የጊዜ ቀደም ተከተልን የሚያመለከቱ ጊዜ ጠቀስ አያያዥ ቃላትና ሀረጋትና 450 ያህል፤ በምድብ ለ (የፀሀፈውን የፅሁፍ አደረጃጀት ስልት) የሚያመላክቱ አያያዥ ቃላትና ሀረጋት 438 ያህል ፤ በምድብ ሐ (ፀህፈው በፅሁፍ ውስጥ ስላሰፈራቸው መረጃዎች ወይም ሀሳቦች … ወዘተ ያውን አተያይ (አመለካከት) የሟያመላክቱ አያያዥ ቃላትና ሀረጋት ደግም 1598 ያህል ሆነዋል፡፡ ከላይ ከቀረቡት የአያያዥ ቃላትና ሀረጋት አመዳደብና - አከፍፈል አኳያ ከተጠኝዎች በብዛት የተጠቀሙበት ምድብ ሐ ሲሆን የተጠቀሙባችው አያያዦች ብዛት 1598(64.28% ) ሆኗል፡፡ በጥናቱ ውጤት መሠረት መምህራንን ከዘመናዊ የአያያዥ ቃላትና ሀረጋት/ ዲስኩር አመልካቶች/ አጠቃቀም አመዳደብና አከፍፈላል ዘዴዎች ጋር ማስተዋወቅ፤ በማስተማሪያ መፃሀፍት ዝግጅትም ሆነ በሰው ኃይል ስልጠና በኩል ከፈተኛ ትኩረት መሰጠት፤ በበቂ ሁኔታ አጋዥ መፃህፍትን ማዘጋጀት፤ መምህራን የተማሪዎችን የድርስት መፃፍ ፍላጎት ለማነሳሳት የተለያዩ ዘዴዎች መጠቀም እንዲሁም የድርሰት መፃፍ ችግሮቻቸን ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ፤ ተማሪዎች፤ በጽሁፎቻቸው ውሰጥ ለሚጠቀሙባቸው አያያዥ ቃላት አገባብ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ፡ የሚሉት በመፍትሔ ሀሳብነት ተሰንዝረዋል፡፡

Description

Keywords

Citation