የጽሁፍ አወቃቀርን ማስተማር አንብቦ የመረዳትን ችሎታ በማጎልበት ረገድ ያለው ሚና፤ በአዲስ ዘመን ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
No Thumbnail Available
Date
2009-06
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋና አላማ የጽሁፍ አወቃቀርን ማስተማር የአንብቦ መረዳትን ችሎታ
ለማጎልበት ያለውን ሚና መመርመር ነበር፡፡ የጥናቱን ተሳታፊዎች ለመምረጥም እድል
ሰጭ ናሙና ዘዴን ተጠቅሟል፡፡ ተሳታፊዎቹም በአዲስ ዘመን ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርትቤት በ2009 ዓ.ም በዘጠነኛ ክፍል ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል በተመረጠው
የናሙና ዘዴ የተመረጡ 52 ተማሪዎች ናቸው፡፡ ጥናቱ ሙከራዊ የምርምር ስልትን
የተከተለና አንድ ተጠኚ ቡድን ብቻ የያዘ የአንድ ቡድን ቅድመና ድህረ ልምምድ
ፈተና ንድፍን ተግባራዊ ያደረገ ነው፡፡ ለተማሪዎች ቅድመ ትምህርት ፈተና ተሰጥቷ፣
ለአምስት ሳምንታት በአጥኚዋ ከተማሩ በኋላ የድህረ ትምህርት ፈተናው ከቅድመ
ትምህርት ፈተናው በተመሳሳይ መልክ ተዘጋጅቶ እንዲፈተኑ ተደርጓል፡፡ ከነዚህ
ተማሪዎችም በቅድመ ትምህርትና በድህረ ትምህርት ፈተናዎችና ከጽሁፍ መጠይቅ
መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹም መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በዳግም
ልኬታ ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልተው በገላጭና ድምዳሜያዊ ስታትስቲክስ
ተተንትነዋል፡፡ በሁለቱ መረጃ መሰብሰቢያዎች አማካኝነት የተገኙት መረጃዎች
በቅድመ ትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት (26.27) እና በድህረ ትምህርት ፈተና
አማካይ ውጤት (33.25) መካከል በስታትስቲክስ ጉልህ ልዩነት (p<0.05) ታይቷል፡፡
ይህም የጽሁፍ አወቃቀር ትምህርት አንብቦ መረዳትን እንደሚያጎለብት አመላክቷል፡፡
የቅድመ ትምህርት የጽሁፍ መጠይቅ አማካይ ውጤት (3.36) እና በድህረ ትምህርት
የጽሁፍ መጠይቅ አማካይ ውጤት (3.7) መካከል በስታትስቲክስ ጉልህ ልዩነት
(p<0.05) መኖሩን አሳይቷል፡፡ ጥናቱ የጽሁፍ አወቃቀር ትምህርት የተማሪዎችን
የጽሁፍ አወቃቀር ግንዛቤ እንዳሻሻለ አሳይቷል፡፡ በጥናቱ ውጤት መሰረትም
የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማጎልበትና ስለ ጽሁፍ አወቃቀር ያላቸውን
ግንዛቤ ለማሻሻል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የጽሁፍ አወቃቀር ትምህርት
የተማሪዎችን የማንበብ ችሎታ የማጎልበት ሚና እንዳለውና የጽሁፍ አወቃቀር
አይነቶችን ለመለየት ጠቃሚ መሆኑን ተገንዝበው ጽሁፉ ለተደራጀበት የጽሁፍ
አወቃቀር ትኩረት ቢሰጡ፣ የመጽሀፍ አዘጋጆች በአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት
ውስጥ የሚካተቱ ምንባቦች የጽሁፍ አወቃቀር አይነቶችን መሰረት ያደረጉ፣ የአንብቦ
መረዳት ጥያቄዎችም የጽሁፍ አወቃቀሩን መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ በማዲረግ
ቢያዘጋጁ፣ ይህ ጥናት ከጽሁፍ አወቃቀር አይነቶች ውስጥ በምክንያትና ውጤት እና
በገለጻ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ከክሂሎች ደግሞ አንብቦ መረዳትን የተመለከተ በመሆኑ
በቀጣይ ሌሎች አጥኚዎች ሁሉንም ጽሁፍ አወቃቀር አይነቶችና ክሂሎች ያካተተ
ጥናት ቢካሄድ የተሻለ ግንዛቤ ሊገኝ ይችላል፡፡ የሚሉ የመፍትሄ ሀሳቦች
Description
Keywords
አንብቦ የመረዳትን ችሎታ