በደቡብ ፤ ብሔር፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ እርከን አማርኛ መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የሰዋስው ትምህርት ይዘት አቀራረብና አደረጃጀት ግምገማ

No Thumbnail Available

Date

2004-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ

Abstract

የዚህ ጥናት አቢይ ትኩረት በደቡብ ብሔር፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ እርከን አማርኛ መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የሰዋስው ትምርት ይዘት አቀራረብና አደረጃጀት ግምገማ ነው፡፡ የዚህ ጥናት አቢይ የመረጃ ምንጭ የሰነድ ግምገማ ሲሆን የጽሁፍ መጠይቅና ቃለመጠይቅ አጋዥ የመረጃ ምንጭ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ጥናቱ በዋናነት አይነታዊ ወይም ገላጭ የምርምር ዘዴን ለመረጃ ትንተናው ተጠቅሟል፡፡በዚህም መሰረት በተተኳሪ መጻህፍቱ ውስጥ የቀረቡ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶችን አቀራረብ ከግልጽነት፤ ከትክክለኛነት ፤ ከተመጣጣኝነትና ከተገቢነት አንጻር ፈትሻል፡፡ እንዲሁም የሰዋሰው ትምህርት ይዘቶቹን አደረጃጀት ከተከታታይነት ፤ ከቀጣይነት/ ተሰጣጣቂነት ፤ ከዝርዝር ወደ አጠቃላይና ከአጠቃልይ ወደ/ ዝርዝር አንጻር ያላችዉን ገጽታ መርምሯል ፡፡ በዚህ ጥናት በመማሪያ መጻህፍቱ ዉሰጥ የቀረቡ የሰዋስዉ ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀቶች በከለሳ ድረሳን ውሰጥ የቀረቡ ጽንስ ሃሳቦች አንጸር እየታዩ የተተነተኑ ሲሆን፤ በናሙናነት ከተመረጡ መምህራንና ተማሪዎች በጽሁፍ መጠይቅ፤ከመጸሀፍቱ አዘጋጀች ደግም በቃለ መጠይቅ በተገኙ ምላሾች ትንታኔውን ለማጠናከር ተምክሯል፡፡ በዚህም መሰረት የሰዋስዋዊ ይዘቶችን አቀራረብ በተመለከተ በአራቱም ተተኳሪ መጻህፍት ውሰጥ ችግሮች መኖራቸውን በተደረገው ፍተሻ ለማረጋጥተችሏል፡፡ በተተኳሪ መጸሀፍቱ ውስጥ የተካቱ የሰዋሰዉ ትምህርት ይዘቶችን አደረጃጀት በተመለከተ ደግም በአራቱም መጻሀፍት ውሰጥ የቀረቡ ሰዋስዋዊ ይዘቶች የአደረጃጀት ችግር እንደሚታይባችው የተደረገዉ ግምገማ ያሳያል፡፡ በመጨረሻም በዚህ ጥናት ውስጥ በሰዋሰው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ላይ የታዪ ድክመቶችን ለማሻሻል ያሰችላሉ ተብሎ የታመነባችዉን የሚከተሉትን የመፍትሄ ሃሳቦች ለመጠቆም ተምክሯል፡- በመማሪያ መጸሀፍቱ ውስጥ በተካተቲ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች ላይ የታዩትን የአቀራረብና የአደረጃጀት እግሮች ለማስወገድ ትኪረት ሰጥቶ መስራት ፤ ተማሪዎችና ልዩ ልዩ የትምህርት ባለሙያዎች ስለ መማሪያ መጸህፍቱ ሰዋስዋዊ ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ያላቸውን አስተያየት መስጠት እንዲችሉን ማመቻችትና ግብረ መልሶቸን በተግባር ላይ ማዋል፤ ወዘተ፡፡

Description

Keywords

Citation