በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ችሎታ ከፆታ አንፃር ንፅፅራዊ ጥናት (በእኖር ኤነር መገር ወረዳ የመገር ወይራ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-10

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናታዊ ጽሁፍአላማ በሴትና በወንድ ተማሪዎች መካከልሀሳባቸውን በጽሁፍ ከመግለጽ አንጻር የተሻሉት የትኞቹ እንደሆኑ ማነጻጸር ነው። በመሆኑም በአማርኛ ቋንቋ ድርሰት የመጻፍ ክሂላቸውን ለማነጻጸር ያስችል ዘንድ መጠናዊ እና አይነታዊ የምርምር ዘዴ በሱ ስር የሚመደበው ገላጭ የአጠናን ዘዴን በመጠቀም እንዱሁም ከመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ደግሞ የችሎታ መለኪያ ፈተናና የጽሁፍ መጠይቅን በመጠቀም የተገኘውን መረጃ ተንትናለች። ተጠኝ ተማሪዎችን በእድል ሰጪ የናሙና አወሳሰድ ዘድን በመጠቀም በጉራጌ ዞን በእኖር ኤነር መገር ወረዳ በመገር ወይራ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 አ.ም ለናሙናነት በተመረጡ ሴት 47 ወንድ 39 በድምሩ 86 ተጠኝ ተማሪዎች እና ሁለት ሴት ሶስት ውንድ በድምሩ አምስት መምህራን ሲካተቱ የችሎታ መለኪያ ፈተና ድርሰት ሲጽፍ የጻፉት ዴርሰት ተነባቢነት የጎደለው በመሆኑ ሴት አንድ (1)ወንድ (3)ሶስት በድምሩ (4) ተማሪዎች በዚህ ጥናት ያልተካተቱ ሲሆኑ ድርሰቱን በትክክል የጻፉ ተማሪዎች ሴት 46 ወንድ36 በድምሩ 82 ተማሪውች በችሎታ መለኪያ ፈተናው የተካተቱ ሲሆኑ የጽሁፍ መጠይቁን በትክክል ያልሞለት ድግሞ ወንድ 3 ተማሪዎች በጥናቱ ያልተካተቱ ሲሆኑ በአጠቃሊይ ሴት 47 ወንድ 36 ድምር 83 ተማሪዎች በጽሁፍ መጠይቁ የተካቱ ናቸው። በመሆኑም ሁለቱን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች በመጠቀም የተፈለገው መረጃ ተሰብስቧል ማለት ነው። የችሎታ መለኪያ ፈተናውን ለተከታታይ ለሶስት ዙር ድርሰት በማጻፍየመጀመሪያውን በመጣልና በቀጣይ ሁለት ተከታታይ የጻፉትን በመውሰድና በሶስት አራሚዎች በማሳረም የተገኘውን ውጤት አስተማማኝነቱን ለማረጋገጥ በቲ ቴስት ስላት ተሰሌቶ የቲ ዋጋ 6.241 አስተማማኝ ሲሆን የፒ ዋጋ ደግሞ 0.000 ልዩነት መኖሩን ሲያመለክት የሜን ድፈረንስ ውጤት ደግሞ 12.104 በመሆኑ ሴት ተማሪዎች ከወንድ ተማሪዎች የላቀ ወጤት ማምጣታቸውን እና ሀሳባቸውን በጽሁፍ ከመግለጽ አንጻር የተሻለ መሆናቸውን ከተገኘው ውጤት ማወቅ እና መረዳት ተችሏል። ሌላው ተማሪዎች የጽሁፍ መጠይቅ የቀረበላቸው 23 ዝግ ጥያቄ (በReliabilityTests) ተሰልቶ የተገኘው ውጤት (0.871) በመሆኑ ትክክለኛነቱ ተረጋግጧል። ከመጠይቁ የተገኘው የመምህራን ውጤት በፐርሰንት እና በአሀዝ ተሰልቶ ሲቀመጥ ከተማሪዎች የተገኘው ምሊሽ ደግሞ በአምስት ዋና ዋና የመጠይቅ ይዘቶች ሲገመገሙ በአራቱ የመመዘኛ መሰፈርቶች ሴት ተማሪዎች ከወንድ ተማሪዎች የተሻለ ሆነው ሲገኙ ከቋንቋ አጠቃቁም አንጻር በተሰላው የቲ ቴስት ወጤት 1.671 ሲሆን የፒ ዋጋ ደግሞ 0.099 አንሶ በመገኘቱ በሁለቱ ጾታዎች መካከል ከግምት የሚገባ ልዩነት አለመኖሩን ያመላክታል። አንጻራዊ በሆነ መልኩ ሲታይ በችሎታ መለኪያ ፈተናውም ሆነ በጽሁፍ መጠይቁ የተገኘው ውጤት የሚያሳየው ሴት ተማሪዎች ከወንድተማሪዎች በተሻለ ሁኔታ ሀሳባቸውን መግለጽ እንደሚችሉከተገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል

Description

Keywords

በአማርኛ ቋንቋ ድርሰት የመጻፍ

Citation