የሸካቾ ብሔረሰብ ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት ክዋኔ
dc.contributor.advisor | አስፋው, ዘሪሁን (ተባባሪ ፕሮፌሰር) | |
dc.contributor.author | ብርሃኑ ተካልኝ, ፍፁም | |
dc.date.accessioned | 2018-06-14T10:33:52Z | |
dc.date.accessioned | 2023-11-09T04:06:43Z | |
dc.date.available | 2018-06-14T10:33:52Z | |
dc.date.available | 2023-11-09T04:06:43Z | |
dc.date.issued | 2006-06 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት በሸካቾ ብሔረሰብ ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት ክዋኔ ላይ የተደረገ ነው፡፡ የጥናቱ አቢይ ዓላማ የብሔረሰቡን ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት ከሞት እስከ ግብዓተ መሬት ፍፃሜ ድረስ ያለውን የአከዋወን ሂደት ማሳየትና መተንተን ነው፡፡ ይህንን እና ሌሎች ዝርዝር ዓላማዎችን ከግብ ለማድረስ መረጃዎች የተሰበሰቡት በሁለት ተፈጥሯዊ አውዶች ላይ ተገኝቶ ምልከታ በማድረግ እና ስለብሔረሰቡ ባህል ጥልቅ መረጃ አላቸው ተብለው ከታመነባቸው የብሔረሰቡ አባላት ጋር ቃለ-መጠይቅ እና የተተኳሪ ቡድን ውይይት በማካሔድ ነው፡፡ ከእነዚህ መረጃዎች የተገኙት ውጤቶች እንደሚያሳዩት የብሔረሰቡ ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት ክዋኔ በሁለት የተለያዩ መልኮች በተለያየ አግባብ እንደሚፈፀም ማወቅ ተችሏል፡፡ በብሔረሰቡ ባህል መሰረት አንድ ጥርስ ያላበቀለ ህፃን ሲሞት መሬት ውስጥ የሚቀበር ከሆነ እናትየው ዳግም ልጅ አትወልድም፤ ማህፀኗ ይደርቃል ተብሎ የሚታመን በመሆኑ ከእናታቸው እቅፍ ሳይወርዱ/ ጥርስ ሳያበቅሉ በሞት የሚነጠቁ ህፃናት የሚቀበሩት በሌላው የዕድሜ ክልል ከሚገኝ የህብረተሰቡ አባል በተለየ በአካባቢው በሚገኝ አንድ ትልቅ ዛፍ ውስጥ ነው፡፡ ሟች በእድሜ የገፋ፣ አንዳች ማህበራዊ ስልጣን ያለው እና ኢኮኖሚያዊ አቅሙ የደረጀ ከሆነ የለቅሶ ስርዓቱ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል ይበልጥ የተለያዩ ክዋኔዎች የሚስተዋሉበት እና የደመቀ ይሆናል፡፡ ሟች ከመቀበሩ በፊት ከአንድ እስከ ሦስት ወር ይቆያል፡፡ ይህም የሚደረገው በዋናነት በየአካባቢው ያሉ የብሔረሰቡ ተወላጆች በቀብሩ ዕለት እንዲገኙ ጊዜ ለመስጠት፣ ለዝግጅት ከወር በላይ የሚፈልገውን ባህላዊ ምግብ እና መጠጥ ለለቀስተኞች ለማዘጋጀት እና በሟች ማሳ ውስጥ መፈፀም ያለባቸውን የእርሻ ስራዎች ለማከናወን መሆኑ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡ በብሔረሰቡ ባህላዊ የለቅሶ ክዋኔ ወቅት በዕድሜ፣ በፆታ እና በማህበራዊ ደረጃ ምክንያት የተወሰኑ ክዋኔዎች ልዩነት መኖሩን የጥናቱ ግኝት ያመለክታል፡፡ በሸካቾዎች ባህል ዋንኛው ለቅሶ የሚከወነው የቀብሩ ዕለት ሲሆን በዚህን ጊዜ ሁሉም እጅጉን መሪር በሆነ ለቅሶ ሟችን የመሰናበት ማህበራዊ ግዴታ አለባቸው፡፡ በጥናቱ የተደረሰበት ሌላው መሰረታዊ ነገር የሸካቾ ብሔረሰብ በቀብሩ ዕለት የሚፈፀመውን መሪር ሀዘን የሚያሳርገው "ጎሞ" በተባለ ባህላዊ ዘፈን እና ጭፈራ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ጭፈራ የሟችን እና የቤተሰቦቹን መልካም ገፅታዎች የሚያወሱ፣ ሞት ለሁሉም የቀረበ ግዴታ መሆኑን የተመለከቱ እና ሞት ዳግም የሟችን ቤተሰቦች እንዳይጎበኝ የሚመኙ ግጥሞች የሚደረደሩበት ነው፡፡ ጭፈራው በከበሮ፣ በክራር እና በጥሩንባ ታጅቦ የሚከወን ሲሆን ዓላማውም የሟች ቤተሰቦች ሀዘን እንዳይጎዳቸው ማድረግ እና "ሞት ሀዘን ሲበዛ ተደጋግሞ የሚመጣ በመሆኑ ሀዘኑ በቅቶን መደሰት ጀምረናል" የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነው፡፡ ብሔረሰቡ ከሌሎች ማህበራዊ አጋጣሚዎቹ ይልቅ ለለቅሶ ስርዓቱ የሚሰጠው ቦታ ከፍ ያለ መሆኑን እና ይህ አጋጣሚ ህብረተሰቡ ማህበራዊ ትስስሩን የሚያጠነክርበት፣ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን የሚገልጥበት፣ አስተሳሰቡን የሚያጎላበት፣ ልዩ ልዩ ባህላዊ እሴቶቹን እና እምነቱን የሚያፀናበትና ከትውልድ ትውልድ የሚያሸጋግርበት መድረክ መሆኑን የጥናቱ ግኝት ያመለክታል፡፡ | en_US |
dc.identifier.uri | http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/895 | |
dc.language.iso | am | en_US |
dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ | en_US |
dc.subject | ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት | en_US |
dc.title | የሸካቾ ብሔረሰብ ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት ክዋኔ | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |